በህዳር ወር 2016 በተያዘው ዌስት ባንክ ኦፌር ወታደራዊ እስር ቤት ውጭ፣ አንድ የእስራኤል ጦር ተሽከርካሪ በእንቅስቃሴ ላይ አያለ ። ኅዳር 21 ቀን በሲፒጄ የተደረገው የታሰሩ ጋዜጠኞች ቆጠራ እንዳመለከተው፣ እስራኤል መስከረም 26 የእስራኤል እና የጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ፣ 17 ጋዜጠኞችን በዌስት ባንክ በማሰሯ 6ኛዋ የጋዜጠኞች አሳሪ እንድትሆን አድርጓታል። ቻይና እና ማይናማር ዋና ዋና አሳሪዎች ከሚባሉት ዝርዝር ውስጥ የቀዳሚነት ስፍራ ይዘዋል። (ፎቶ፤ ኤኤፍፒ/ፋደል ሳና)

የ2016 የታሰሩ ጋዜጠኞች ቆጠራ: የታሰሩ የጋዜጠኞች ቁጥር ቀድሞ ወደነበረው ክብረ-ወሰን ተጠግቷል፤ እስራኤል ውስጥ ያለው እስራት አሻቅቧል