14 results
በአርሊን ጌትዝ መስከረም 26፣ 2016 የእስራኤል እና የጋዛ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ፣ እስራኤል በዓለም ላይ ግንባር ቀደም የጋዜጠኞች አሳሪ አገር ሆና ብቅ እንዳለች የ2016 የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ (ሲፒጄ) ቆጠራ አሳይቷል። ከቻይና፣ ከማይናማር፣ ከቤላሩስ፣ ከሩሲያ እና ከቬትናም (እንደቅደም ተከተላቸው) ቀጥሎ፣ እስራኤል፣ ከኢራን እኩል የስድስተኛነትን ደረጃን ይዛለች። Available in: በአጠቃላይ፣ ሲፒጄ ህዳር 21፣ 2016 ባደረገው ቆጠራ 320 ጋዜጠኞች…
በጄኒፈር ደንሃም/ሲፒጄ ምክትል ኤዲቶሪያል ዳይሬክተር ጥር 5፣ 2014 የታተመ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲፒጄ) በዓመቱ በሰበሰበው አጠቃላይ መረጃ፣ በ2013/14 ቢያንስ 27 ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ መገደላቸውን እና ህንድ እና ሜክሲኮም ብዙ የሚዲያ ሰራተኞች ከተገደሉባቸው ሀገራት መካክል ቀዳሚ መሆናቸውን አስታውቋል። በፕሬስ ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ያካተተው የሲፒጄ ሪፖርት ከታተመ ከህዳር 30፣ 2014 ወዲህ፣ የተገደሉት የጋዜጠኞች ቁጥር በሦስት…
በመላው ሀገሪቱ ውጥረት በነገሰበት ሁኔታ፣ በመጭው ሰኔ አጋማሽ አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ፣ ኢትዮጵያ ቀን ቆርጣለች። በትግራይ ውስጥ በህዳር ወር የተከሰተው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው። የሚዲያ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ በሌሎች በርካታ ክልሎችም፣ በብሔሮችና ጎሳዎች መካካል በሚፈጠር ግጭት እና በተቃውሞዎች የተነሳ፣ መጠነ-ሰፊ ነውጦች እና ዘግናኝ አደጋዎች ታይተዋል። የሲፒ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ከህዳር 22፣ 2013 ጀምሮ፣ ቢያንስ ሰባት የሚሆኑ ጋዜጠኞች ዘብጥያ…
በዓለም ላይ የታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥር በ2013/14 ሌላ አዲስ “ክብረ-ወሰን” አስመዝግቧል። አዲስ የቴክኖሎጂ እና የደህንነት ህጎችን በመጥቀስ፣ከእስያ እስከ አውሮፓ እስከ አፍሪካ ያሉ አፋኝ መንግስታት በነጻው ፕሬስ ላይ አስከፊ እርምጃ ወስደዋል። በኤዲቶሪያል ዳይሬክተር አርለን ጌትስ የቀረበ የሲፒጄ ልዩ ዘገባ። ህዳር 30፣ 2014 የታተመ ኒው ዮርክ ይህ ዓመት ለፕሬስ ነፃነት ተሟጋቾች በተለየ ሁኔታ በጣም አስከፊ ጊዜ ነበር። በ2013/14…
ቻይና በዓለም ላይ እጅግ አስከፊ ጋዘጠኞችን አሳሪ በመሆን ቀጥላለች፤ ህንድ እና ሜክሲኮ አስቃቂ አሳሪ ከሚባሉት ሀገሮች ከመጀመሪያዎቹ ተርታ ተሰልፈዋል። ኒውዮርክ ህዳር 30 2014— በ2013/14 እስር ቤት ውስጥ የታጎሩ የጋዜጠኞች ቁጥር አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል፤ 293 ጋዜጠኞች ለእስር የተዳረጉበት ይህ ዓመት፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና በሚዲያ ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች በዓለም ዙሪያ እየተስፋፋ በመጣ ቁጥር፣ ገለልተኛ ዘገባዎችን…
በሙቶኪ ሙሞ አውሎ ሚዲያ ሴንተር የተሰኘው የኢትዮጵያ ኦንላይን የዜና አውታር የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድን አስተዳደር በመተቸቱ ከመንግስት በሚደርስበት “ጫና እና መሰናክል” የተነሳ ድርጅቱን ዘግቶ ሰራተኞቹን በሙሉ ለማሰናበት መገደዱን በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በፌስቡክ ገፁ ባሰፈረው ልጥፍ አስታውቋል። የሚዲያ ሪፖርትስ እና የሲፒጄ ዘገባ እንደሚያስረዳው፣ ድርጅቱ የተዘጋው፣ በሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ በርካታ የአውሎ ሚዲያ ሴንተር ጋዜጠኞች እና…
የኢንተርኔት መዘጋት ለፕሬስ ነፃነት ከባድ መዘዝ እንዳለው እና ጋዜጠኞችንም ስራቸውን በብቃት ለማከናዎን አዳጋች እያደረገባቸው እደሆነ ሲፒጄ አረጋግጧል። ኢንተርኔት ተዘጋ ወይም ተገደበ ማለት፣ የሚዲያ ሰራተኞች አንድ ሁነት እስኪፈጠር ድረስ ምንጮችን ማግኘት፣ የመረጃን እውነታ ፍተሻ ማድረግ ወይም ታሪኮችን መሰነድ አይችሉም ማለት ነው። ኢንተርኔት ሊዘጋ የሚችለው ባብዛኛው በግጭት፣ በፖለቲካ አለመረጋጋት ወይም በምርጫ ወቅቶች ሲሆን፣ እንደ አክሰስ ናው (Access…
በሪቤካ ሬድሌሞር/የሲ.ፒ.ጄ ኦዲየንስ ኢንጌጅመንት አስተባባሪ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ላይ በተደረገው የካፒቶል የዓመጽ ሰልፍ ዙሪያ ምርመራ እየተካሄደ ባለበት ሁኔታም፣ አሁን ድረስ ስለ አሜሪካ ምርጫ የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ አሳሳቢነት እንደቀጠለ ነው፡፡ ይህን አይነት ክስተት እየተጋፈጠች ያለቸው ግን አሜሪካ ብቻ አይደለችም፡፡ በተለይ እንደ ብሄራዊ ምርጫ ካሉ ታላላቅ ሁነቶች ጋር በተያያዘ የሀሰትኛ መረጃ ስርጭት በዓለም ዙሪያ እየተከሰተ ነው፡፡ የበዝፊድ ኒውስ…
የዲጂታል ደህንነት ኪት በመጨረሻ የተሻሻለው፣ ሚያዚያ 13 2013 ዓ.ም ጋዜጠኞች የወቅቱን የዲጂታል ደህንነት ዜናዎችን እና እንደ ምንተፋ (hacking)፣ ፊሺንግ (phishing) እና ክትትልን (surveillance) ባሉ ስጋቶች ላይ የሚወጡ ወቅታዊ መረጃዎችን በመከታተል ራሳቸውንና የመረጃ ምንጮቻቸውን መከላከል አለባቸው፡፡ ጋዜጠኞች ሃላፊነት ሰለወስዱበት መረጃና መረጃው ባልተገባ ሰው እጅ ቢገባ ምን ሊፈጠር እንደሚችል በማሰብ አካውንቶቻቸውን፣ መሣሪያዎቻቸውን፣ ግንኙነቶቻቸውን እና የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎቻቸውን…
መስከረም 18 ቀን፣ 2013 የተሻሻለ በተሳሳተ መረጃ፣ በሴራ ንድፈ ሀሳቦች ወይም በሀሰተኛ ዜናዎች ላይ ሪፖርት የሚያደርጉ ጋዜጠኞች እነዚህን አመለካከቶች በሚያመነጩ ወይም በሚደግፉ፣ ወይም ደግሞ ጠንካራ የፖለቲካ ዝንባሌ ባላቸው ሰዎች አማካኝነት የመረብ ላይ ጥቃት ተጋላጭ ይሆናሉ። የዚህ ዓይነቱን መረጃ በመስመር ላይ ማሰራጨትን የሚደግፉ ሰዎች፣ ጋዜጠኞችን ከመስመር ላይ ግንኙነት ለማስወጣት እና ተአማኒነታቸውን ለማጉደፍ የተቀናጁ ጥቃቶችን ሊያደራጁ ይችላሉ።…