ከሮይተርስ ጋዜጠኛው ዳኒሽ ሲዲኪ ፎቶ አጠገብ ሻማዎች ተለኩሰዋል። ጋዜጠኛው ሀምሌ 10፣ 2013 አካባቢ ቪጊል በምትባል ህንድ ኒው ዴሊህ ውስጥ በምትገኝ ቦታ ላይ በአፍጋኒስታን ሃይሎች እና በታሊባን መካከል ህንድን ከፓኪስታን በሚያዋስናት ድንበር ማቋረጫ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት ሲዘግብ ተገድሏል። በሲፒጄ ጥናት መሰረት በ2014 ቢያንስ 27 ጋዜጠኞች በስራቸው ምክንያት ተገድለዋል።(ሮይተርስ/አኑሽሪ ፋድናቪስ)

በፕሬስ ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች፤  በ2013/14 ከሁሉም በላይ ጋዜጠኞችን የገደሉ ሀገሮች

በጄኒፈር ደንሃም/ሲፒጄ ምክትል ኤዲቶሪያል ዳይሬክተር

ጥር 5 2014 የታተመ

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲፒጄ)  በዓመቱ  በሰበሰበው አጠቃላይ መረጃ፣ በ2013/14 ቢያንስ 27 ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ መገደላቸውን እና  ህንድ እና ሜክሲኮም ብዙ የሚዲያ ሰራተኞች ከተገደሉባቸው ሀገራት  መካክል ቀዳሚ መሆናቸውን አስታውቋል።  በፕሬስ ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ያካተተው የሲፒጄ  ሪፖርት ከታተመ ከህዳር 30፣ 2014 ወዲህ፣ የተገደሉት የጋዜጠኞች ቁጥር በሦስት ከፍ ብሏል።  በግፍ ከተገደሉት 27 ጋዜጠኞች መካከል፣ ሀያ አንዱ ለሞት የተዳረጉት፣  ዘገባ በመስራታቸው የበቀል ግድያ/ እርምጃ ተወስዶባቸው ነው።  ሌሎች አራቱ  የተገደሉት፣ በግጭት ቀጠናዎች የዘገባ ስራ እየሰሩ ሲሆን፣ ሌሎች ሁለት ጋዜጠኞች  ደግሞ  የኋላ ኋላ ወደ ደም መፋሰስ ያመሩ ተቃውሞዎችን  ወይም የጎዳና ላይ ነውጦችን በመዘገብ ላይ እያሉ ነው ህይዎታቸው ያለፈው።

ሲፒጄ፣ አሁንም የ6 የሜክሲኮ ጋዜጠኞችን ጨምሮ የሌሎች 18 ጋዜጠኞች ግድያ ከስራቸው ጋር የተያያዘ መሆን አለመሆኑን  ለመበየን ምርመራ እያደረገ ነው።

በ2012/13፣ 32 የነበረው አጠቃላይ የጋዜጠኞች ግድያ ቁጥር ቢቀንስም፣ የተረጋገጡት የአጸፋ ግድያዎች ቁጥር በአመዛኙ በተመሳሳይ መልኩ ቀጥሏል፤ ይህም ጋዜጠኞች የጥቃት ኢላማ ሆነው መቀጠላቸውን ያመላክታል። ህንድ እና ሜክሲኮ አራት እና ሶስት የተረጋገጠ ግድያን በተዋረድ በማስመዝገብ ግንባር ቀደም ገዳዮች የሆኑ ሀገራት በመሆን በሲፒጄ በዓለም-አቀፍ ያለመከሰስ ኢንዴክስ (Global Impunity Index)  ላይ ተካትተዋል፤ ይህ ኢንዴክስ፣ የፕሬስአባላትንተነጥለው ለነፍስ ግድያ የሚፈለጉበት፣  ባንጻሩ ወንጀለኞች እንዲሁ በነጻ የሚለቀቁባቸው ሀገራትን ዝርዝር ቀልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።

በማያንማር፣ የወታደራዊው ጁንታው በፕሬስ ላይ በወሰደው ጭካኔ የተመላበት እርምጃ፣ ቢያንስ ሁለት ጋዜጠኞች ከመገደላቸውም በላይ፣ እስከ ህዳር 22፣ 2014 ድረስ ቢያንስ 26 ጋዜጠኞች በዘገባ ስራቸው ምክንያት ለእስር ተዳርገዋል። በታህሳስ ወር ብቻ የተፈጸሙት እነዚህ ሁለት ግድያዎች፣ ከ1991 ጀምሮ በምያንማር ለተፈጸመው የጋዜጠኞች ግድያ የሲፒጄን ዓመታዊ ከፍተኛ ቁጥር ይወክላሉ።  በዚህም የተነሳ፣ ሲፒጄ በ2013/14 ባካሄደው የታሰሩ ጋዜጠኞች  ቆጠራ፣ ሀገሪቱ፣ ከቻይና ቀጥላ በአለም ሁለተኛዋ አሰከፊ የጋዜጠኞች አሳሪ መሆኗን መርዳት ተችሏል ።

ሲፒጄ፣ በጋዜጠኞች ግድያ ላይ ባደረገው ጥናት ያገኛቸው ሌሎች ግኝቶች ደግሞ የሚከተሉትን ያካትታል፤

  •  በ2013/14 እንደ ፀረ-መንግስት ፓርቲዎች ወይም ተቃዋሚዎች ያሉ የፖለቲካ ቡድኖች በጋዜጠኞች ላይ ጥቃት በማድረስ ዋነኞቹ  ተጠርጣሪዎች የነበሩ ሲሆን፣ ፖለቲካ ደግሞ ከዚያም የባሳው አደገኛው ገዳይ ነበር።
  • የአፍጋኒስታን የቴሌቪዥን ምሶሶ የነበረችው እና በሰኔ ወር በካቡል ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ አጥቂዎች በተሳፈረችበት መኪና  ላይ የተጣበቀን ፈንጂ በማፈንዳት የተገደለችው ሚና ኻይሪ በ 2013/14 የግድያ ኢላማ መ ብቸኛዋ ሴት ጋዜጠኛ መሆኗ ተረጋግጧል።  የየመን ፎቶ ጋዜጠኛ የነበረችውና በወቅቱ ነፍሰ ጡር የነበረችዋ  ሌላዋ ዘጋቢ ራሻ አብዱላህ አል-ሃራዚም እንዲሁ ጥቅምት 30፣ 2014 መኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ነው የተገደላቸው፤ ይሁንና፣ ጥቃቱ ያነጣጠረው፣ በፍንዳታው ክፉኛ በተጎዳው በባለቤቷ ጋዜጠኛ  ማህሙድ አል-አቲ ላይ እንደነበረ ይታመናል።
  • አብዛኛዎቸ የተገደሉት ጋዜጠኞች በሀገራቸው ዜናዎችን ሲዘግቡ የነበሩ የአካባቢው ተወላጆች ናቸው።  በ2013/14 ዓ.ም፣ ሶስት ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ተገድለዋል፤ አንደኛው፣ በሐምሌ ወር በአፍጋኒስታን ሀይሎች እና በታሊባን መካከል የነበረውን ግጭት  በመዘገብ ላይ እያለ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት  ቆየት ብሎ አፍጋኒስታን ውስጥ ህይወቱ ያለፈው ህንዳዊው የፎቶ ጋዜጠኛ፣ ዳኒሽ ሲዲኪ ነው፤ ሊሎቹ ደግሞ፣ ሚያዝያ ወር በቡርኪናፋሶ ታፍነው የተገደሉት  የስፔን ዘጋቢ ፊልም ቡድን አባላት የነበሩት ዴቪድ ቤሪያን እና ሮቤርቶ ፍራይል ናቸው።
  • በየካቲት ወር የተገደለው ሊባኖሳዊው ጋዜጠኛ ሎክማን ስሊም በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ በ2013/14 ካጋጠሙት ክስተቶች መካከል የተረጋገጠው ብቸኛው የጋዜጠኛ ግድያ ነው። ይህም፣ ባለፉት አስር አመታት በክብረ-ወሰንነት ተይዞ ከነበረው የክልሉ  ከፍተኛ የጋዜጠኞች ሞት አንጻር፣ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ያሳያል።

በ2013/14 ስለተገደሉ እና ስለታሰሩ ጋዜጠኞች የሲፒጄን መረጃ ከኢንተራክቲቭ ካርታችን (interactive map) እና  አመታዊ የታሳሪ ጋዜጠኞ ቆጠራ ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።

የጥናቱ ዘዴ

ሲፒጄ፣ የጋዜጠኞችን ሞት በተመለከተ ዝርዝር ዘገባዎችን ማጠናቀር የተጀመረው በ1985 ነበር። የሲፒጄ ሰራተኞች ከእያንዳንዱ ሞት ጀርባ ያለውን ሁኔታ በገለልተኛነት በመመርመር ስለሁኔታው ማረጋገጫ ይሰጣሉ።  ሲፒጄ አንድ ግድያ ከጋዜጠኝነት ጋር የተገናኘ ነው ብሎ መደምደሚያ ላይ የሚደርሰው፣ የሲፒጄ ሰራተኛው፣ ጋዜጠኛው ወይም ጋዜጠኛዋ  የተገደሉት በስራቸው የተነሳ  ቀጥተኛ የሆነ የበቀል እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብሎ ሲያረጋግጥ፤  ጋዜጠኛው ከውጊያ ጋር በያያዘ ተኩስ ልውውጥ ሲገደል፤ ወይም  ጋዜጠኛወ ወደ ሁከት የተቀየረ የተቃውሞ ሰልፍን  ለመዘገብ በአደገኛ የስራ ስምሪት  እያለ ህይወቱ ካለፈ ብቻ ነው።

የግድያው አላማ  ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ፣ ጋዜጠኛው ከስራው ጋር በተያያዘ ሞቶ ሊሆን ይችላል ብሎ ካሰበ፣ ሲፒጄ፣ ጉዳዩን “ያልተረጋገጠ” የሚል  ፍረጃ  በመስጠት የማጣራት ሂደቱን ይቀጥላል።

አደጋው የተከሰተው በጥላቻ/በተንኮል ካልሆነ በስተቀር፣  በህመም የሞቱ፣  በመኪና ወይም በአውሮፕላን አደጋ የተነሳ  ህይዎታቸው ያለፈ ጋዜጠኞች በሲፒጄ ዝርዝር  ውስጥ አይካተቱም። የተለያዩ መመዘኛዎችን የሚጠቀሙ ሌሎች የፕሬስ ድርጅቶች የተለያዩ የሟቾችን ቁጥር ይጠቅሳሉ።

የሲፒጄ በ2013/14 የተገደሉ ጋዜጠኞች  የመረጃ ቋት በእያንዳንዱ ተጎጂ ላይ የካፕሱል ሪፖርቶችን እና መረጃውን   ለመመርመር የሚያስችሉ ማጣሪያዎችን ያካትታል። ሲፒጄ፣ ከ1984 አንስቶ የተገደሉትን ሁሉንም ጋዜጠኞች እና የተሰወሩ ወይም በስራቸው ምክናያት  የታሰሩትን ጋዜጠኞች የያዘ የመረጃ ቋት አለው።

ጄኒፈር ደንሃም የሲፒጄ ምክትል የአርትኦት ዳይሬክተር ናቸው። ሲፒጄን ከመቀላቀላቸው በፊት የፍሪደም ሃውስ

ነፃነት በአለም እና የፕሬስ ነፃነት ዘገባ የምርምር ዳይሬክተር ነበሩ።