ጃፓናዊው ጋዜጠኛ ዩኪ ኪታዙሚ፥ በመስሉ ላይ በየካቲት ወር ወደ ያንጎን ፖሊስ ጣቢያ ሲወሰድ የሚታየው፥ የምያንማር ድህረ-ወታደራዊ መፈንቅለ ተከትሎ ከታሰሩ በርካታ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ነው። ኪታዙሚ የውሸት ዜና በማሰራጨት ተከሷል፣ ነገር ግን በግንቦት ወር ወደ ጃፓን እንዲመለስ ተፈቅዶለታል። ምያንማር አሁን ከቻይና ቀጥላ በዓለም ሁለተኛዋ የጋዜጠኞች አሳሪ አገር ነች። (ምስል በኤፒ)

በዓለም አቀፍ ደረጃ በእስር ቤት የታጎሩ ጋዜጠኞች ቁጥር ጨምሯል

በዓለም ላይ የታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥር በ2013/14 ሌላ አዲስ “ክብረ-ወሰን” አስመዝግቧል። አዲስ የቴክኖሎጂ እና የደህንነት ህጎችን በመጥቀስ፣ከእስያ እስከ አውሮፓ እስከ አፍሪካ ያሉ አፋኝ መንግስታት በነጻው ፕሬስ ላይ አስከፊ እርምጃ ወስደዋል። በኤዲቶሪያል ዳይሬክተር አርለን ጌትስ የቀረበ የሲፒጄ ልዩ ዘገባ።

ህዳር 30፣ 2014 የታተመ

ኒው ዮርክ

ይህ ዓመት ለፕሬስ ነፃነት ተሟጋቾች በተለየ ሁኔታ በጣም አስከፊ ጊዜ ነበር።  በ2013/14 በእስር ቤት የተካሄደው ቆጠራ በስራቸው ምክንያት የታሰሩት ጋዜጠኞች ቁጥር 293 እንደ ደረስ አሳይቷል፤ ይህም  አዲስ የአለም ክብረ-ውሰን ሆኖ ተመዝግቧል። በ2012/13 ከነበረውና ተስተካሎ ከተመዝገበው የ280 የታሳሪዎች ዝርዝር ሲነጻጸርም ጭማሪ አሳይቷል። በ2013/14  የስራ ዘመን የዘገባ ስራ በመስራታቸው ብቻ፣ እስካሁን ቢያንስ 24 ጋዜጠኞች ተገድለዋል። ሌሎች 18 ጋዜጠኞች ደግሞ የጥቃቱ ኢላማዎች እነሱ መሆን አለመሆናቸው ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ህይዎታቸውን አጥተዋል።

50 ያህል ጋዜጠኞችን እስር ቤት በማጎር፣ ቻይና፣ በተከታታይ ለሶስተኛ አመት ከሁሉ የከፋች አሳሪ ሀገር ሆናለች። የጥር 24 2013ቱን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ በሚዲያ ላይ በወሰደችው አስከፊ እርምጃ የተነሳ፣ ማይናማር ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ብላለች። ግብፅ፣ ቬትናም እና ቤላሩስ በተዋረድ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች ቁጥር ያላማሳለስ እየጨመረ የመጣበት ምክንያት (ሲፒጄ ባካሄደው ቆጠራ ቢያንስ 250 እስረኞችን ያስመዘገበበት ተከታታይ ስድስተኛ አመት መሆኑን ልብ ይሏል) ከአገር አገር ይለያያል። ይሁን እንጅ፣ በሁሉም ዘንድ የሚንጸባረቅ አንድ ግልጽ አዝማሚያ አለ፤ ለገለልተኛ ዘገባ ትግስት የማጣት ሁኔታ እያደገ መምጣት። የልብ ልብ የተሰማቸው ባለስልጣናት ራሳቸውን በስልጣን ለማቆየት ፍትሃዊ ሂደቶችን ችላ እያሉ እና አለም አቀፍ ደንቦችን እየጣሱ ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ እንደ ኮቪድ-19 እና የአየር ንብረት ለውጥ ላሉ ጉዳዮችን ቅድሚያ በመስጠት እየተሰራ ባለበት ሁኔታ፣ ጨቋኝ መንግስታት በሰብአዊ መብት ረገጣ ምክንያት ሊመጣ የሚችለው ህዝባዊ ቁጣ የደበዘዘ እንደሆነ ያውቃሉ። በሌሎች አጣዳፊ ጉዳዮች የተጠመዱ ዲሞክራሲያዊ መንግስታትም ፖለቲካዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማድረግ  እምብዛም ፍላጎት እነደሌላቸው ይረዳሉ።

እርግጥ ነው አንዳንድ ያልተጠበቁ አገሮች ብዙ ጋዜጠኞችን ወደ እስር ቤት የማስገባቱን አካሄድ ቀይረውታል። በአንድ ወቅት በዓለም ላይ እጅግ የከፋ የጋዜጠኞች እስር ቤት የነበረችው ቱርክ ባለፈው አመት 20 እስረኞችን ከፈታች በኋላ፣ በሲፒጄ ቆጠራ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አሥራ ስምንት ያልተፈቱ የጋዜጠኞች ይቀሯታል። ሳውዲ አረቢያም 10 እስረኞችን ለቃለች፤- በ 2013/14ቱ የህዝብ ቆጠራ ወቅት ተካተው ከነበሩት 14 ጋዜጠኞች ውጪ ሌሎች አዲስ ጋዜጠኞችን አላሰረችም። ያን ማድረጓ ከመጀመሪያዎቹ አምስቱ ታላላቅ አሳሪዎች ተርታ አስወጥቷታል።

ይሁን እንጂ፣ ዝቅተኛ የእስረኛ ቁጥር ማስመስገብን በፕሬስ ላይ የአመለካከት ለውጥ መምጣቱን እንደማመላከቻ አድርጎ ማየት የዋህነት ነው። ሲፒጄ እንዳመለከተው፣ በ2008 የከሸፈውን መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከትሎ፣ ቱርክ በሚዲያ ላይ በወሰደችው አስከፊ እርምጃ የተነሳ የሀገሪቱን ዋና ዋና ሚዲያዎች ደብዛ አጥፍታቸዋለች ማለት ይቻላል፤ ብዙ ጋዜጠኞችም ሙያውን ለቀው እንዲወጡ ተገፋፍተዋል። መንግስት ብዙ ጋዜጠኞች ባመክሮ እንዲፈቱና ለፍርዱ ውሳኔ ይግባኝ በፈቀደ መጠን በቱርክ እስር ቤት ያሉ የጋዜጠኞች ቁጥርም እየቀነሰ መጥቷል።

በሳውዲ አረቢያ፣ በ2011 የተፈጸመው አስፈሪው የጀማል ካሾጊ አሰቃቂ ግድያ እና አካል መገነጣጠል በ2012 ከተካሄደው በርካታ አዳዲስ እስራት ጋር ተዳምሮ፣ ከአዳዲስ የእስር ማዕበል በበለጠ ሁኔታ ጸጥ እንዳስኛቸው መገመት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪም፣አምባገነን መሪዎች ገለልተኛ ዘጋቢዎችን እና ማሰራጫዎችን ለማገድ የሚያስችሉ ከማሰር ይበልጥ የተራቀቁ መንገዶችን እየተጠቀሙ ነው። ጋዜጠኞችን ለእስር ከመዳረግ ይልቅ፤ ኢንተርኔትን መዝጋት እና በከፍተኛ የቴክኖሎጂ እና በስፓይዌሮች አማካኝነት ጋዜጠኞችን መሰለል ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ ዘዴዎች ናቸው።

ቻይና ውስጥ የሚታየው ጋዘጠኞችን በማያቋርጥ መልኩ እስር ቤት ማጎር አዲስ አይደለም። ሆኖም፣ ሆንግ ኮንግ ውስጥ የታሰሩ  ጋዜጠኞች በሲፒጄ አመታዊ ቆጠራ የተካተቱት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፤ የዚህ ምክንያት ደግሞ፣ በከተማይቱ ውስጥ የተካሄዱት ታሪካዊ የዲሞክራሲ ደጋፊዎች ተቃውሞዎች ምላሽ እንዲሆን በ2012 የተደነገገው የብሄራዊ ደህንነት ህግ ነው።

የአፕል ዴይሊ እና የኔክስት ዲጂታል መስራች እና የሲፒጄ 2013/14 ግዌን ኢፊል ፕሬስ ፍሪደም ተሸላሚ(Gwen Ifill Press Freedom Awardee) የሆኑትን ጂሚ ላይን ጨምሮ፣ ስምንት የሆንግ ኮንግ የሚዲያ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል። ይህም ቀድሞውንም ችግር ላይ ለነበረው የከተማይቱ ነጻ ፕሬስ ግልጽ የሆነ ፈተና ነበር።  አንዳንዶችም የእድሜ ልክ እስራት ሊገጥማቸው ይችላል።

በዋናዎ የቻይና ግዛት፣ ሌሎች ጋዜጠኞች ብዙ የተድፈነፈኑ ኦርዌሊያዊ ክሶች (Orwellian charges) ይገጥሟቸዋል። በግሏ የምትሰራው ዣንግ ዛን  የተባለችው የቪዲዮ ጋዜጠኛ በግንቦት ወር 2012፣ ቻይና ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሰጠችውን ምላሽ አስመልክቶ ባቀረበችው ሂሳዊ ሽፋን የተነሳ በግንቦት ወር 2012 ለእስር ተዳርጋላቸ፤ የቀረባባት ክስም “ጠብ ማንሳት እና ችግር መፍጠር” የሚል ሲሆን ለአራት አመታት ተፈርዶባት እስር ላይ ትገኛለች፤ – የዚህ አይነቱን ክስ፣ የገዥው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ  ሰላማዊ ተቺዎችን ለማጥቃት ብዙውን ጊዜ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው። ሌሎች ጋዜጠኞች ደግሞ የተከሰሱት “ባለሁለት ፊት” ተብለው ሲሆን፣ ይህ አይነቱ ክስ ህጋዊ መሰረት የሌለውና በኮሚኒስት ፓርቲ ላይ ስውር ተቃውሞን የሚያመለክት እና ብዙ ጊዜ የዚንጂያንግ ኡገር ጋዜጠኞችን (Xinjiang’s Uighur journalists) ለማጥመድ የሚያገለግል ክስ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ቻይና ጋዜጠኞች ያልሆኑ፣ ነገር ግን ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ግንኙነት አላቸው የምትላቸውን ዒላማዋ ውስጥ አስገብታለች፤ በዚህ ረገድ፣ ፋሉን ጎንግ ከተባለው መንፈሳዊ ቡድን ጋር ግንኙነት ላለው ዘ ኢፖክ ታይምስ (The Epoch Times) የሚዲያ ኩባንያ መረጃዎችን አቀብላችኋል በሚል፣ 11 ሰዎችን አስራለች። እነዚህ 11 ግለሰቦች በሲፒጄ የታሳሪዎች ቆጠራ ውስጥ አልተካተቱም፤ ይህም የሆነው፣ ዘ ኢፖክ ታይምስ ሰዎቹ የኔ ጋዜጠኞች አይደሉም በማለቱ ነው፤ ይሁንና፣ የእነርሱ መታሰር ቻይና የሚዲያ ንግግሮችን ለማፈን የምታደርገውን ጥረት የሚያሳይ አሳዛኝ አመላካች ነው።

እስከ ህዳር 22፣ 2013 ድረስ በእስር ቤቶቿ ውስጥ ምንም ጋዜጠኞች ያልነበሯት ማይናማር፣ የወታደራዊው መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎ በጋዜጠኞች ላይ በተፈጸመ አፈና፣ ከ12 ወራት በኋላ 26 ጋዜጠኞችን ለእስር ዳርጋለች። ይሁን እንጂ፣ ሁኔታው  ይህ ቁጥር ከሚያሳየው በላይ የከፋ ነው።አሜሪካዊው ዳኒ ፌንስተርን ጨምሮ  ብዙ ጋዜጠኞች ከወራት እስር በኋላ፣ ከሲፒጄ ቆጠራው በፊት የተለቀቁ ሲሆን፣ የሲፒጄ ጥናት እንደሚያመለክተው ሌሎች በእስር ላይ እንደ ዘጋቢ ያልታወቁ ጋዜጠኞች ሊኖሩ ይችላሉ። በተጨማሪም፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ጋዜጠኞች ተሸሽገዋል ወይም ተሰደዋል– የእነዚህ ጋዜጠኞች አገር ጥሎ መሄድ በሀይል ከስልጣን በተወገደው እና በህዝብ በተመረጠው መንግስት ዘመን ተገኝቶ የነበረውን የገለልተኛ ሚዲያ ጠቀሜታ የሚበትን ነው።

በ2013/14 ግብፅ 25 ጋዜጠኞችን በማሰር ከማያንማር በመቀጠል ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች። ይህ አኅዝ ምንም እንኳን ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የቀነሰ ቢሆንም፣ እየተካሄዱ ያሉት እስራቶች የአብደል ፋታህ ኤል ሲሲ መንግስት ለሀገሩን ህግጋት ቁብ የሌለው መሆኑን የሚያሳይ ነው።

የግብፅ ባለስልጣናት ተጨማሪ ክሶችን በማቅረብ የእስረኞች ቅድመ ችሎት የእስራት ጊዜ ከሁለት አመት መብለጥ የለበትም የሚለውን አዘውተረው ህግ እየተላለፉ ጊዜውን ይለጥጡታል። በሌሎች ሁኔታዎችም ደግሞ፣ የቅጣት ፍርዳቸውን ያጠናቀቁ እስረኞችን ለመፍታት ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀምጡባቸዋል።

ለምሳሌ፣ ሻውካን በመባል የሚታወቀውን የግብፅ ፎቶ ጋዜጠኛ እና የሲፒጄ አለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ተሸላሚ ማህሙድ አቡ ዘይድ ከቶራ እስር ቤት የካቲት 25 2011 ከተለቀቀ አንስቶ ሌሊቱን በፖሊስ ጥበቃ ስር እያሳለፈ ይገኛል። “በፖሊስ እይታ ስር” በሚል ቅድመ ሁኔታ ስለተፈታ፣ ለቃጣዮቹ አምስት አመታት በየምሽቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየሄደ ሪፖርት ማድረግ አለበት። ሌሊቱንም በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ባለው ማሰሪያ ክፍል እንዲያድር የፖሊስ ት ዕዛዝ ተላልፎበታል። ሸዋካን፣ ገንዘቡንና እና ንብረቱን ለአምስት ዓመታት እንዳያስተዳድርም ተከልክሏል።

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ትልቁ የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ማነቆ የታየው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። በ2010 ዓ.ም.፣ ታይቶ በማይታወቅ ዘመን የመጣ ተሃድሶን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሰየሙት የአብይ አህመድ መንግስት በ2013/14 ዓ.ም. ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሃገሮች መካከል ከኤርትራ ቀጥሎ ሁለተኛው እጅግ አስከፊው የጋዜጠኞች አሳሪ ሆኗል።

ከአንድ አመት በፊት በፌደራል መንግስት ሃይሎች እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሚመራው ሃይሎች መካከል የእርስ በርስ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንሰቶ፣ በሀገሪቱ በርካታ ጋዜጠኞች ታስረዋል። እስከ ህዳር 22 2013 ዓ.ም.ድረስ፣ ዘጠኝ ዘጋቢዎች በእስር ላይ ናቸው። ስድስቱ ደግሞ በህዳር ወር ግጭቱ እየበረታ ሲሄድ እና መንግስት ሀይለኛ አስቸኳይ ጊዜ ህጎችን በደነገገበት ጊዜ የታሰሩ ናቸው። ሲፒጄ፣ በዓመቱ ውስጥ ሌሎች በርካታ የፕሬስ ነፃነት ጥሰቶችን ሰንዷል።

ይህ በእንዲህ እንዳላ፣ የቤላሩሱ መሪ አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ለህዝብ አስተያየት ምንም ዴንታ እንደሌላቸው እና በስልጣን ላይ ለመቆየት ያለቸወን ፍላጎት ለማሳካት፣ ጋዜጠኛ ራማን ፕራታሴቪችን ለማሰር በወሰዱት ከልክ ያለፈ እርምጃ  አሳይተዋል፡ ፕራታሴቪችን በቁጥጥር ስር ለማድረግ፣ የሪያን የህዝብ ማጓጓዣ አውሮፕላንን በአጸያፊ ሁኔታ ጠለፋ አካሂደዋል

ቤላሩስ አሁን 19 ጋዜጠኞችን እስር ቤት አጉራለች። ይህም ባለፈው አመት ከነበረው 10 የጋዜጠኞች ታሳሪ ቁጥር የጨመረ ሲሆን፣ ሲፒጄ በ1985 በእስር ላይ ስላሉ ጋዜጠኞች መረጃ መያዝ ከጀመረ ወዲህ ከፍተኛው አሃዝ ነው።

በእስር ላይ ከሚገኙት አንዱ የገለልተኛ ስፖርት ዜና ጣቢያ ትሪቡና ጋዜጠኛ አሊያክሳንደር ኢቫሊን ነው። ኢቫሊን፣ የህዝብን ፀጥታ በማናጋት ተከሶ አራት አመት ተፈርዶበት በእስራት ላይ እያለ ከአድናቂዎቹ አንዱ በኢቫሊን የአከባቢ እግር ኳስ ክለብ ግጥሚያ ላይ 25 ቁጥር ያለው የክለብ ማሊያ ለብሶ በመጫወቱ፣ ለ14 ቀናት በእስራት ተቀጥቷል። ምክንያቱም፣ ይህ ቁጥር ኢቫሊን ለክለቡ ሲጫወት የሚለብሰው ቁጥር በመሆኑ ነው።

ሃሳብን በነፃነት መግለጸ ጥቁር ጥላ ባጠላበት በዚህ አመት፣ እንደዚህ አይነቱ በፕሬስ ነፃነት ላይ የሚደረግ ትዕግስት ማጣት፣ በክፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ያለውን የጋዜጠኞች እስር ለመቀነስ ያለውን የተስፍ ጭላንጭል ያመነምነዋል።

ስሌሎች ግኝቶች ማስተዋሻ

  • እስክ ህዳር 22  2014 ድረስ ሥራቸውን በመስራትቸው በተወሰደ የበቀል ርምጃ 19 ጋዜጠኞች መገደላቸውን ሲፒጄ ዘግቧል፤ በመላው 2013  የተገደሉት ደግሞ 22 ጋዜጠኞች ነበሩ።  ከዚህ በተጨማሪ፣ ከታህሳስ 2013 እስክ አሁን ባለው ጊዜ ሌሎች ሶስት ጋዜጠኞች ከግጭት ቀጠናዎች በዘገባ ስራ ላይ እያሉ ሲገደሉ፣  ሌሎች ሁለት ጋዜጠኞች ደግሞ በስተመጨረሻ ወደ ዘግናኝ ሁኔታ የተቀየረን  የጎዳና ላይ ሁከት በመዘገብ ላይ እያሉ ህይወታቸውን አጥተዋል።
  • በምዕራቡ ንፍቀ ክበብ ከሚገኙ ሀገሮች ሜክሲኮ ለጋዜጠኞች  በጣም አደገኛ ሀገር እንደሆነች ቀጥላለች። የዘገባ ስራ በመስራታቸው አጸፋዊ መቀጣጫ በሚመስል አኳኋን ሶስት ጋዜጠኞች ተገድለዋል፤  የሌሎች ስድስት ጋዜጠኞች አማሟት ከጋዜጠኝነት ስራቸው ጋር ግንኙነት  ያለው መሆን አለምሆኑን  ለማጣራት ሲፒጄ  የምረመራ ስራ እያካሄደ ነው።
  • ህንድ፣ሥራቸውን በመስራታቸው ብቻ በተወሰደ የበቀል እርምጃ መገደላቸው የተረጋገጠባት ከፍተኛ፡ የጋዜጠኞች ቁጥር ያላት (ማለትም አራት ጋዜጠኞች) ሀገር ሆናለች።  ሌላ አምስተኛ ጋዜጠኛ ደግሞ  የተቃውሞ ሰልፍ በመዘገብ ላይ እያለ ተገድሏል።
  • በላቲን አሜሪካ  በተደረገ የእስር ቤቶች ቆጠራ  ስድስት ጋዜጠኞች እስር ላይ እንዳሉ ታውቋል፡፡ ከእነዚህ መካከል፣ ሶስቱ በኩባ፣ ሁለቱ  በኒካራጓ፣ አንዱ ደግሞ በብራዚል እስር ቤቶች ያሉ ናቸው።  በአንፃራዊነት ሲታይ ይህ ክልል  ዝቅተኛ የታሳሪ ጋዜጠኞች ቁጥር ያለው ቢሆንም፣ የፕሬስ ነፃነቱ በአሳሳቢ ሁኔታ እያሽቆለቆለ እንደመጣ  የሲፒጄ ጥናት ያሳያል።
  • ቢያንስ 17 በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች የሳይበር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።  በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቤኒን፣ ሁለት ጋዚጠኞች፣ ግልጽነት የጎደልውን የዲጂታል ህግ ተላልፋችኋል በሚል ክስ ተመሰርቶባቸዋል፤ ይህ ህግ፣ በመስመር ላይ  ምንም ነገር ማሳተምንም ሆነ ማሰራጨትን በወንጀል እንደሚስከስስ ስለሚፈቀድ፣ በፕሬስ ነፃነት ላይ የተጋረጠ ዋነኛ  ተግዳሮት ሆኗል።
  • ታስረው ከነበሩት 290 ጋዜጠኞች መካክል አርባዎቹ (ከ14% በታች ማለት ነው) ሴቶች ናቸው።
  • የታሳሪ ጋዜጠኞች የቆጠራ ቀነ ገደብ በተጠናቀቀበት ወቅት፣ በሰሜን አሜሪካ አንድም ጋዜጠኛ እስር ላይ አልነበረም። ይሁን እንጅ፣ የሲፒጄ አጋር የሆነው የአሜሪካ  የፕሬስ ነፃነት አነፍናፊ (U.S. Press Freedom Tracke) 2013/14 በመላው አሜሪካ 56 ጋዜጠኞች ለእስር እንደተዳረጉ መዝግቧል።  ከዚህ ውስጥ፣ 86 በመቶው የሚሆነው  እስር የተፈጸመው በተቃውሞ ወቅት ነው። ካናዳ ውስጥ፣ በሰሜናዊ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ውስጥ ከመሬት ይዞታ መብት ጋር በተያያዘ  የተቃውሞ ሰልፍን  ሲዘግቡ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሁለት ጋዜጠኞች፣ ፍርድ ቤት ቀርበው በቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ከመወሰኑ በፊት፣ ለሶስት ሌሊት በእስር እንዲቆዩ ተደርገዋል።

የጥናቱ ዘዴ

የታሰሩ ጋዜጠኞች ቆጠራ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ ጋዜጠኞችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን፣ የተሰወሩትን  ወይም መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት የታገቱትን አያካትትም። ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ የሆኑት “የጠፉ” ወይም “የተጠለፉ” በሚል ምድብ ተካተዋል።

ለሲፒጄ፣ ጋዜጠኛ ማለት በማንኛውም ሚዲያ ዜናን የሚዘግብ ወይም በሕዝብ ጉዳይ ላይ በሚዲያ አስተያይት የሚሰጥ ሰው ማለት ሲሆን የሚዲያ አይነትም የሕትመት፣ የፎቶግራፍ ፣ የሬዲዮ፣ የቴሌቪዥን እና የመስመር ላይ ሚዲያን ያካትታል።  ሲፒጄ በሚያካሂደው ዓመታዊ የእስር ቤቶች ቆጠራ  የሚካተቱት ጋዜጠኞች ከሥራቸው ጋር በተያያዘ የታሰሩ መሆናቸው የተረጋገጠላቸውን ብቻ ነው ።

የሲፒጄ ዝርዝር ያካተተው እስከ ኅዳር 22 ቀን 2014 እስከ እኩል ቀን ድረስ በእስር ላይ የነበሩ ጋዜጠኞችን ነው።  በዓመቱ ውስጥ ሲታሰሩና ሲፈቱ የነበሩ የብዙ ጋዜጠኞችን ዝርዝር  አይጨርም። የእነዚህ ጋዜጠኞች ጉዳዮች በሲፒጄ ድረ-ገጽ (http://cpj.org) ላይ ይገኛሉ። ጋዜጠኞቹ ከእስር መለቀቃቸውን ወይም በእስር ላይ መሞታቸውን ድርጅቱ በማያጠራጥር መልኩ እስከሚያረጋግጥ ድረስ፣ ስማቸው በሲፒጄ ዝርዝር ውስጥ እንደተካተተ ይቆያል።

አርሊን ጌትዝ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (ሲፐጄ) አርቶዖት ዳይሬክተር ናት። ባሁኑ ሰዓት መቀመጫዋን በኒውዮርክ ያደረገችው ጌትዝ  በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእስያ እና በመካከለኛው ምስራቅ የውጭ ዘጋቢ እና አርታኢ እንዲሁም  ለሮይተርስ፣ሲኤንኤን እና ለኒውስ ዊክ አርቶኦት አስፈጻሚ (editorial executive) ሆና ሰርታለች።