A picture taken on October 1, 2019, shows the logos of mobile apps Instagram, Snapchat, Twitter, Facebook, Google, and Messenger. (AFP/Denis Charlet)
የእጅ ስልክ ላይ የሚገኙ የኢንስታግራም፣ የስናፕቻት፣ የጉግልና የሜሴንጀር አርማዎችን የሚያሳይ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም. የተነሳ ፎቶ (ኤ.ኤፍ.ፕ/ ዴኒስ ቻርሌት)

የዲጂታል ደህንነት፤ የታለሙ የመስመር ላይ ጥቃቶችን መከላከል

መስከረም 18 ቀን፣ 2013 የተሻሻለ

በተሳሳተ መረጃ፣ በሴራ ንድፈ ሀሳቦች ወይም በሀሰተኛ ዜናዎች ላይ ሪፖርት የሚያደርጉ ጋዜጠኞች እነዚህን አመለካከቶች በሚያመነጩ ወይም በሚደግፉ፣ ወይም ደግሞ ጠንካራ የፖለቲካ ዝንባሌ ባላቸው ሰዎች አማካኝነት የመረብ ላይ ጥቃት ተጋላጭ ይሆናሉ። የዚህ ዓይነቱን መረጃ በመስመር ላይ ማሰራጨትን የሚደግፉ ሰዎች፣ ጋዜጠኞችን ከመስመር ላይ ግንኙነት ለማስወጣት እና ተአማኒነታቸውን ለማጉደፍ የተቀናጁ ጥቃቶችን ሊያደራጁ ይችላሉ። እነዚህን ጉዳዮች የሚዘግቡ የሚዲያ ሰራተኞች በመስመር ላይ  የሚደርሰውን ጉዳት ለመገደብ የመስመር ላይ መገለጫቸውን (online profile) ለመቆጣጠር እና አካውንቶቻቸውን ለመጠበቅ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ።

የመረብ ላይ አሻራዎን ይቆጣጠሩ

የተቀናጁ የመረብ ላይ ጥቃት ፈጻሚዎች በቀጥታ እርስዎን ኢላማ ለማድረግ ራሳቸውን ያደራጃሉ። ይህ  ቅንጅት በማኅበራዊ ሚዲያ መረብ ጣቢያዎችዎ በኩል እና ስለእርስዎ የግል ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በመስመር ላይ የህዝብ የመረጃ ቋቶችን የሚመለከቱ ብዙ ሰዎችን ያካትታል። ጥቃት አላሚዎቹ፣ እርስዎን ወይም የቤተሰብዎን አባላት ለማስፈራራት የግል መረጃዎን (ለምሳሌ አድራሻዎትን) ሊጠቀሙ ይችላሉ። በተጨማሪም፣ አጥቂዎቹ ፎቶዎችዎን አፈላልገውና እንደሚፈልጉት አዛብተው እርስዎን ለማዋከብ፣ ለማንቋሸሽ ወይም ለማሳፈር ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

 • በበይነመረብ ላይ ስለእርስዎ ምን መረጃ እንደሚገኝ ይፈትሹና፣ ይህ መረጃ የተያዘባቸውን ጣቢያዎች በውል ያጢኗቸው።
 • ለሕዝብ ማጋራት የማይፈልጉትን ወይም ለአደጋ ሊያጋልጠኝ ይችላል ብለው የሚያስቡትን እንደ አድራሻ ወይም የልጆች ፎቶግራፍ ያለ ማንኛውንም መረጃ ለማስወገድ እርምጃዎችን ይውሰዱ፡፡
 • በበይነመረብ ላይ ምን ዓይነት ምስሎች እንዳሉዎት ይዎቁና ምስሎቹ እርሰዎን ለማጥቃት እንዴት መጠቀሚያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ።
 • አድራሻዎ ከህዝብ የመረጃ ቋቶች እንዲወገድ ወደ መረጃ ማስወገጃ ጣቢያዎች (data removal sites) ይመዝገቡ::
 • ስለርስዎ ሌሎች ሊያገኙት  የሚችሉት ምን መረጃ እንዳለ ለማየት የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶዎቸውን የግላዊነት ቅንብሮች (private settings) ይፈትሹ። እርስዎን ለማጥላላት ሊያገለግል ይችላል ወይም አደጋ ላይ ሊጥለኝ ይችላል ብለው የሚያስቡትን ይዘት ያስወግዱ ወይም ይገድቡ፡፡
 • ለማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች የአካባቢ መከታተያ አገልግሎትን (location tracking) ያጥፉ፡፡
 • የቆዩ የማህበራዊ ሚዲያ ፖስቶችን መሰረዝ ወይም የድሮ ትዊቶችን ማጥፋት የሚያስችል አገልግሎትን ይጠቀሙ። ካሁን በፊት የለጠፏቸውን ፖስቶች እንደገና እንደ አዲስ በመጠቀም፣ ስም አጥፊዎች እርስዎን ለማጥላላት ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ ይገንዝቡ።
 • ማንኛውንም የተለመዱ የፊደል ግድፈቶችን ጨምሮ፣ ስምዎ በጠቀሰ ቁጥር ማወቅ የሚያስችሎዎትን የጉግል ማንቂያዎችን ያዘጋጁ፡፡
 • የመስመር ላይ መገለጫዎን በመደበኛነት እንዲገመግሙ ለማስታወስ የሚያስችል የቀን መቁጠሪያ አስታዋሾችን (ለምሳሌ፣ በየሦስት ወሩ ሊሆን ይችላል) ያዘጋጁ፡፡
 • በመስመር ላይ ያለዎትን የማንኛውም መረጃ ቅጅ ካስወገዱት በኋላም እንኳ፣ መረጃው በኢንተርኔት ላይ በተወሰነ መልኩ (ለምሳሌ በይነመረብ መዝገብ ቤት አገልግሎቶች) ውስጥ ሊኖር እንደሚችል ልብ ይበሉ።

የአካውንቶችዎን ደህንነት ይጠብቁ

የመስመር ላይ አጥቂዎች አካውንቶችዎን ለማግኘትም ሊሞክሩ ይችላሉ። ይህን የሚያደርጉት፣ ስለእርስዎ የግል መረጃ ለማግኘት፣ አካውንተውን ለመክፈት እንዳይችሉ በመቆለፍ እና ስምዎን ሊያጠፋ የሚችል ይዘት በእርስዎ አካውንት ስም ለማውጣት ነው፡፡ የአካውንቶቻችዎን ደህንነት መጠበቅ ለማረጋገጥ፣ ጋዜጠኞች  የሚከተሉትን እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ከተቻለ፣ እነዚህ እርምጃዎች መወሰድ ያለባቸው ጥቃት ከመከሰቱ በፊት ነው።

 • ኢሜሎችን፣ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን እና የገንዘብ ሂሳብዎ የሚያንቀሳቅሱበትን አካውንት ጨምሮ ለሁሉም አካውንቶችዎ ባለ ሁለት-ደረጃ ማረጋገጫን (two-factor authentication,2FA) ያብሩ።
 • ለሁሉም አካውንቶችዎ ለየት ያሉና ከ20 በላይ ፊደላት ያሏቸው ረጅም የይለፍ ቃሎችን ለመፍጠር የይለፍ ቃል አስተዳደርን (password manager) ይጠቀሙ።
 • አካውንቶችዎን በመከታተል፣ ያልተለመደ እንቅስቃሴ በሚከሰት ጊዜ ማስጠንቀቂያዎችን ማግኘት እንዲችሉ  የመስመር ላይ አገልግሎት ሰጪዎች (online service providers) ይጠቀሙ፡፡
 • በመስመር ላይ ያሉ መረጃዎችዎን ይነጣጥሉ። የማህበራዊ ሚዲያ አካውንትዎን፣ ለሥራ ወይም ለግል ጉዳይ ብቻ ያውሉ፡፡ ለምሳሌ፣ በፌስቡክ አካውንትዎ ላይ፣ የቤተሰብዎ አባላትን ለስራ ጉዳይ እና ለግል ጉዳይ በሚጠቀሙባቸው አካውንቶች ጓደኛ እንዲሆኑዎ አያድርጉ፡፡ ይህ ማለት፣ አንድ አጥቂ አካውንተዎን መድፈር ቢችል፣ ስለግል ህይውተዎና ስል ስራ ህይውተዎ መረጃን ባንድ ጊዜ ማግኘት አይችልም ማለት ነው፡፡
 • በጥቃት ወቅት የተወሰኑትን ወይም ሁሉንም የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶችዎን ውሱን ለማድረግ ያስቡ፡፡

ከሌሎች ጋር ይነጋገሩ

ለበይነመረብ የጅምላ ትንኮሳዎች ኢላማ ሆኛለሁ የሚል ስጋት ካደረበዎ፣ ስለ ሁኔታው ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ ይንገሯቸው። ይህንን ማድረግ፣ ሊከሰት ስለሚችለው ጥቃት እንዲዘጋጁና ጥቃቱንም እንዴት እንደሚከላከሉት ለማወቅ ያግዘዎታል። በተጨማሪም፣ የሚከትከሉትን እርምጃዎች ለመውሰድ ያስቡ፤

 • የአካውንት ቁጥርዎን ሊረከቡልዎ የሚችሉ እና በመስመር ላይ ትንኮሳ የተነሳ ሊፈጠርብዎ ስለሚችለው መገለል ድጋፍ ሊሰጡዎ ለሚችሉ ባልደረቦች፣ ጓደኞች እና የቤተሰብ አባላት ትስስር ለመፍጠር ያስቡ፡፡
 • ስለ በይነመረብ ትንኮሳዎች ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ መንገርን ያስቡ፡፡ የመስመር ላይ አጥቂዎች ብዙውን ጊዜ በቤተሰብ አባላት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው፤ ስለሆነም፣ ከማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቻቸው ውጭ የሚመጣን ግንኙነት እንዴት እንደሚቀንሱ መማር ግድ ይላቸዋል።
 • የሚጠቀሙበት ማህበራዊ ሚዲያ፣ ትንኮሳን በተመከለተ ምን አይነት ፖሊሲ እንዳለው ይወቁ። በሥራ ላይ እያሉ ስለሚድርስብዎ ትንኮሳ ምን አይነት ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉም ከአርታኢይዎ እና ከቡድንዎ ጋር ይነጋገሩ።

ከተንኳሾች ጋር ሰለሚደረግ ግንኙነት

ለተንኳሾችዎ ምላሽ መስጠት ብዙውን ጊዜ ሁኔታውን ሊያባብስ ይችላል፡፡ በታለመ የመስመር ላይ ጥቃት፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኢንተርኔት አጥቂዎች ጋዜጠኞች የሚሰጧቸውን አስተያየቶች፣ ቀጥተኛ መልዕክቶች እና ኢሜሎች ብዛት መከታተል አይችሉም ማለት ነው፤ እናም የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶቻችዎን ለስራ መጠቀም አይችሉም፡፡ አያሌ የመስመር ላይ ጥቃት አድራሾች ሲያጋጥም፣ የሚከትሉትን  እርምጃዎችን መውሰድ ይበጃል፤

 • የኢንተርኔት ላይ ተንኳሾች እርስዎን ሊቃወሙ እንደሚፈልጉ እና ምላሽ ከሰጧቸውም ትንኮሳቸውን አባብሰው ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ።
 • እርስዎን ሊያጠቁ የመጡ አካውንቶች ሁሉ ህያዋን ሰዎችን የሚዎክሉ እንዳልሆኑ ይገንዘቡ፡፡ አንዳንዶቹ አውቶማቲክ አካውንቶች ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ ተከፍሏቸው ሰዎችን ለማዋከብ በመስመር ላይ የተሰማሩ  ህያዋን ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
 • ትንኮሳን በተለይም ማንኛውም አስፈሪ መስሎ የሚሰማዎትንና ወደ አካላዊ ጥቃት ያመራል ብለው የሚያስቡትን ጥቃት ለመሰነድ የሚያስችል ስርዓት ይፍጠሩ፡፡ እንዲሁም፣ በመደበኛነት እርስዎን የሚያጠቁዎትን አካውንቶችን መዘግበው ይያዙ። ዛቻዎቹ በደህንነትዎ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱበዎ እንደሆነ ከተሰማዎት፣ ተግቢውን እርዳታ ይጠይቁ።
 • የጥቃት መልዕክቱን ወይም ምስሉን ጨምሮ፣ ቀኑን፣ ሰዓቱን እና የተንኳሹን ስም ወይም  የአጥቂውን መለያ በስክሪንሾት ያንሱ። ከሚዲያ ተቋምዎ ወይም ከባለስልጣናት ጋር ስለጉዳዩ በሚነጋገሩብት ጊዜ  ሊጠቅመዎ ስለሚችል ጥቃቱ የተፈጸመበትን የጊዜ ሰሌዳ (time series) መዝግበው ይያዙ።
 • የሚያስጨንቁዎትን አካውንቶች ማገድ ወይም ድምጻቸውን ማጥፋት መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ልብ ይበሉ፡፡ የሚደርስብዎትን በደል ለማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሪፖርት ካደረጉ፣ ቅሬታዎን ያቀረቡበትን ቀንና ሰዓት በማስታወሻዎ መዝግበው ይያዙ።
 • በትዊተር ላይ አላስፈላጊ ምላሽ እንዳይገኙ አድርገው ይዝጉት። በእንዲህ አይነት ሁኔታ ለቲዎቶችዎ ምላሽ መስጠት የሚችሉት እርስዎ የሚከተሏቸው ሰዎች ብቻ ናቸው።
 • አንዴ ጥቃቱ ከተወገደ፣ ከጥቃቱ ጀርባ ማን እንደነበረና እርስዎ ላይ ያነጣጠረበት ምክንያት ምን እንደነበረ ማጣራት ሊያስፈልግዎ ይችላል።
 • የመስመር ላይ መገለጫዎን ደህንነት እንዴት ማረጋግጥ እንድሚችሉ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ፣ “የግል መረጃዎን ከኢንትርኔት ማስወገድ” የሚለውን ድረገጽ ይመልከቱ። እቤትዎ ሆነው በሚሰሩበት ጊዜ የበለጠ ደህንነተዎን እንዴት ማስጠበቅ እንደሚችሉ የሚያሳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኝት፣ ስለ ኮቪድ-19 ሽፋን የሚሰጠውን የሲፒጄ “ዲጂታል ደህንነት አማካሪ” ያንብቡ።