ሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓ.ም፣ የህግ አስከባሪ አካላት በስራ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞችን ሚኒሲክ፣ ቤላሩስ ውስጥ ሲያስሩ የሚያሳይ ፎቶ፤ የፎቶው አንሺ ከታስሩት የሮይተርስ ጋዜጠኞች አንዱ ሲሆን ፎቶውን ያነሳውም እርሱ እራሱ ከመታስሩ ጥቂት ቀደም ብሎ ነው (ሮይተርስ/ ቫስሊ ፌዶሴንኮ)

የአካል እና ዲጂታል ደህንነት – እስር እና በእስር መቆየት

የፈላጭ ቆራጭ አገዛዞች ወይም ሀይለኛ ወታደራዊ እና የፖሊስ አስተዳድር ባሉባቸው ሀገራት በመሄድ እንደ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ እንደ ሙስና ወይም የእርስ በእርስ ግጭቶች ያሉ የዜና ስራዎችን በሚዘግቡብት ወቅት፣ ለእስራት ሊጋለጡ ይችላሉ።

እንዲህ ባላ ጊዜ፣ ከባለሥልጣናቱ ዘንድ ተቃዎሞ ሲያጋጥመዎ፣ ተቃዎሞው ሕጋዊ ባይሆንም እንኳ ለደህንነትዎ ሲባል፣ እነርሱ የሚሉዎትን መስማት ብልህነት ነው፡፡

ደህንነታቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ ይችሉ ዘንድ፣ ጋዜጠኞች የሚከተሉትን የዲጂታል እና የአካል የደህንነት ምክሮችን ሊያጤኑ ይገባል፡፡

የዲጂታል ደህንነት ምክር

አስቀድሞ የመሳሪያዎትን እና የመረጃዎችዎን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ቅድመ-ጥንቃቄ  እርምጃዎችን መውሰድ፣ ሌሎች ስለ እርስዎ እና ስለ ምንጮችዎ መረጃ የማግኘት እድላቸውን ይቀንሰዋል።

መሣሪያዎችዎን ስለ ማዘጋጀት

ለእስር ከተዳረጉ፣ መሣሪያዎችዎ ሊወረሱ እና ሊበረበሩ ይችላሉ፡፡

በመሆኑም፣ የመሣሪያዎን እና የመረጃዎችዎን ደህንነት ለመጠበቅ የሚከተሉትን እርምጃዎች ይውሰዱ፤

  • መሣሪያዎን በፒን መቆለፊያ ወይም በይለፍ ቃል ይሰሩ፡፡ ይሁንና፣ እነዚህ ቁልፎች ባለሥልጣናትን መሳሪያዎትን ከመክፈት ሊያግዷቸው እንደማይችሉ ልብ ይበሉ፡፡
  • ሪፖርት በሚያደርጉበት ሀገር ውስጥ ምስጠራን ስለመጠቀም የወጣውን ህግ አውቀው ኮምፒውተሮችዎ እና አንድሮይድ መሣሪያዎችዎ ላይ ያለውን የምስጠራ ቁልፍ/መተግበሪያ ማብራት እንዳለብዎ ይገንዘቡ። በቅርብ ጊዜ የወጣው አይፎን ምስጠራን እንደ መስፈርት ያካትታል። ምስጠራውን ለማንቃት መሣሪያዎን ማጥፋት ይኖርብዎታል።
  • ሰነዶች እና ፎቶዎችን ጨምሮ በመሳሪያዎችዎ ውስጥ ምን መረጃ እንዳለ እና በየትኛው ቦታ ላይ እንደ አስቀመጧቸው ያስታውሱ። ለአደጋ ሊያጋልጠኝ  ይችላል የሚሉትን  መረጃ ሁሉ ያስወግዱ ፡፡
  • መረጃዎቸዎን አዘውትረው እንደ ሃርድ ድራይቭ ባሉ የውጫዊ ማከማቻ መሣሪያ ላይ ይገልብጡ።  በመቀጠልም፣  የገለበጧቸውን መረጃዎች ከመሣሪያዎ ላይ ይሰርዙ። ያም ሆኖ፣ የተራቀቀ የቴክኖሎጂ አቅም ያላቸው ባለሥልጣናት ወይም የወንጀል ቡድኖች የሰረዙትን ፋይል መልሰው ማግኘት እንደሚችሉ ይወቁ፡፡
  • የውጭ ማከማቻ መሳሪያዎችዎን ያመስጥሩ፡፡ የመረጃዎችዎን ቅጂዎች ከአንድ በላይ በሆነ ድራይቭ ላይ ማስቀመጥ እና ከተቻለም መሳሪያዎችዎ ሊገኙ በማይችሉበት ቦታ፣ ማለትም ከቤትዎ ወይም ከቢሮዎ  ውጭ በተለየ ቦታ ማስቀመጥ ጥሩ ዘዴ ነው፤ ያንን ማድርግ የሚገባዎ፣ እርስዎ ቢታሰሩ፣ ቤትዎ እና ቢሮዎ መፈተሻቸው ስለማይቀር ነው።
  • የአሰሳ ታሪከዎን አዘውትረው በማጥፋት፣ ሁልጊዜም  ከሁሉም አካውንቶች ይውጡ፡፡
  • በመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያዎችዎ ውስጥ ምን ይዘት እንዳለ ለይተው በማወቅ፣ ይዘቱን አዘውትረው መገልበጥ እና መሰረዝ የሚያስችሉ ሁኒታዎችን ያመቻቹ፡፡
  • በስልክዎ እና በመልዕክት መላኪያ መተግበሪያዎችዎ ውስጥ ያሉትን ዕውቂያዎች ይቆጣጠሩ፡፡ እርስዎን ወይም እነሱን አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ የሚሏቸውን ሰዎች ዝርዝር መረጃዎች ያስወግዱ፡፡ እውቂያዎች በመተግበሪያዎች እና ክላውድ ውስጥ እንዲሁም በሲም ካርዱ ላይ ተከማችተው እንደሚቆዩ ልብ ይበሉ።
  • መሳሪያዎችዎን ከርቀት ለማጽዳት እንደሚችሉ አድርገው ያዘጋጁ፡፡ ምንአልባት ብያዝ ወይም ብታሰር እና በርቀት መሳሪያዎቼን ለማጽዳት ጊዜ አይኖርኝም የሚል ስጋት ካለዎት፣ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ሃላፊነት ወስዶ ከርቀት ያጸዳልኛል ብለው ከሚያምኑት ሰው ጋር አስቅድመው መነጋገር ይኖርብዎታል፡፡ አንድ መሣሪያን ከርቀት ማጽዳት የሚቻለው ከበይነመረብ ጋር ወይም ከተንቀሳቃሽ ስልክ ዳታ ጋር ከተገናኘ ብቻ ነው። መሣሪያዎን ማጽዳት የበለጠ ተጠርጣሪ ሊያደርግዎት እንደሚችልም ልብ ይበሉ።
  • ከእይታዎ ርቀው ቆይተው ከቀናት በኋላ  ሊመለሱለዎት የሚችሉ መሳሪያዎችዎ፣ በስፓይዌር ተበክለው ሊሆን ይችላል። እንደዚህ ባላ ጊዜ፣  ከተቻለ አዳዲስ መሣሪያዎችን ይግዙ። ይኽ የማይቻል ከሆነ ደግሞ፣ ስልከዎን ዳግም የማስጀመር ስራ (factory reset) ያከናውኑ፤ ይኽን ማድረግ ግን ስፓይዌሩን ሊያስወግደው እንደማይችል ልብ ይበሉ።

አካውንቶችዎን መጠበቅ

እርስዎ በቁጥጥር ስር ከዋሉ፣ የበይነመረብ አካውንቶችዎን የይለፍ ቃሎች  እንዲያስረክቡ ሊጠየቁ ይችላሉ። ምንም እንኳን አካውንቶችዎን እንዳይጠቀሙባቸው ሰዎችን መከልከል ባይችሉም፣ ማየት የሚችሉትን የመረጃ መጠን ለመገደብ የሚያስችል  የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ፡፡

አካውንቶችዎ ውስጥ ያለውን ይዘት ማግኘት የሰዎች አቅም ይገድቡ፤

  • በሁሉም አካውንቶችዎ በተለይም በኢሜል እና በማህበራዊ አውታረመረቦች ውስጥ ያለውን ይዘት አዘውትረው ይፈትሹ። የትኛው መረጃ እርስዎን ወይም ሌሎችን ለአደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል ይወቁ፡፡
  • የድሮ ኢሜሎችን እና ማህበራዊ ሚዲያ መልዕክቶችን ጨምሮ በእነዚህ አካውንቶች ውስጥ ያሉ ይዘቶችን አዘውትረው ምትክ ውስጥ እያስቀመጡ ይሰርዙ፡፡ ይህን በማድረግ፣  መልዕክቶችን ከእራስዎ አካውንት ብቻ እንጅ መልክቶቹን ከላኩላቸው ሰዎች አካውንቶች ውስጥ መሰረዝ እንደማይቻል ልብ ይብሉ። እርስዎ የሚጠቀሙባችው እንደ ሲግናል ወይም ዋትስአፕ ያሉ አገልግሎቶች ጫፍ እስከ ጫፍ እስካልተመስጠሩ ድረስ፣ ኢሜሎችን እና መልዕክቶችን ጨምሮ የሁሉም መረጃዎችዎ ቅጅ በኩባንያው ተጠብቆ ይያዛል፤ ለመንግስታትም ተላልፎ ሊሰጥ ይችላል፡፡
  • የማኅበራዊ ሚዲያ መለያዎችዎ በተከታዮችዎ እና በጓደኞችዎ ዝርዝር አማካኝነት ብዙ መረጃን ይሰጣ፡፡ ይህ መረጃ የግል እና ሙያዊ የግንኙነት ትስስሮቸዎን ለመሳል ሊያገለግል ይችላል፡፡ በማህበራዊ አውታረመረቦች ላይ ያሉ ጓደኞችዎን እና ተከታዮችዎን እየፈተሹ፣  ለአደጋ ሊያጋልጠኝ  ብለው የሚጠረጥሩትን ማንኛውንም ሰው ከተከታየወቸዎ  ዝርዝር ውስጥ ያስወግዱ። የዚህ መረጃ ቅጅ አሁንም በኩባንያው አገልጋይ/የመረጃ ቋት ላይ የሚገኝ ሲሆን በመንግስት ተላልፎ ሊሰጥ ይችላል፡፡
  • በኢንተርኔት ላይ ባሉ አገልግሎቶች ውስጥ የተያዙ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች እንደ የቤተሰብ አባላት ያሉ  የግል እውቂያዎችን እንዲሁም የሙያ እውቂያዎችን ጨምሮ የመረጃ ምንጮችን ለመለየት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይወቁ።
  • ከአካውንቶችዎ በመውጣት እና የአሰሳ ታሪክዎን አዘውትረው በማጽዳት፣ የአካውንቶችዎን በሰዎች የመገኘት እድል ይበልጥ አዳጋች ያድርጉ፡፡ በስልክዎ ወይም በኮምፒተርዎ ላይ የሚገኙ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያዎችን እና የኢሜል አገልግሎቶችን መጠን ገደብ ያብጁለት፡፡

የአካል ደህንነት ምክር

ከምደባ በፊት መታሰብ ያለበት

  • ሪፖርት በሚያደርጉበት ሀገር ውስጥ እንደ ጋዜጠኛነትዎ የሚሰጡዎትን ህጋዊ መብቶች ምን እንደሆኑ በመመርመር ለይተው ይወቁ። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትንም እንደዚሁ፤
  • ምን ሊያሳስርዎ እንደሚችል ወይም እንደማይችል፤
  • ካሁን በፊት የታሰሩ የጋዜጠኞች እስር እና ሰለአያያዛቸው ሁኒታ፤
  • የትኞቹ የደህንነት አካላት (ማለትም ዩኒፎርም የለበሱ ፖሊሶች፣ ሲቪል ለባሽ ስውር መኮንኖች፣ የሰራዊቱ አባላት ወ.ዘ.ተ) በቁጥጥር ስር ሊያውሉዎ እንደሚችሉ፤
  • ከመከሰሰዎ በፊት ለምን ያህል ጊዜ ሊታሰሩ እንደሚችሉ፤
  • ስልክ ለመደወል እንደሚፈቀድልዎ ወይም እንደምይፈቀድልዎ እና ለማን መደወል እንደሚችሉ፤
  • ቋንቋዎን ሊናገር የሚችል ጠበቃ ወይም ሕጋዊ ተወካይ ማግኘት እንደሚችሉ ወይም እንደማይችሉ፤
  •  ለጠበቃ ወይም  ለህጋዊ ተወካይ የሚከፈለውን  ወጭ ማን እንደሚሸፍን፤
  • ኤምባሲዎ ወይም ቆንስላዎ ስለ እስርዎ መረጃ የሚደርሰው እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ   (አግባባና ኖሮት ሲገኝ)፤
  • ከታሰሩ የት ሊወሰዱ እንደሚችሉ፤
  • ተጨማሪ ቁሳቁሶችን (ለምሳሌ የሳተላይት ስልኮች፣ ለግርግር ጊዜ የሚያገልግሉ መነጋገሪዎች (walkie talkies) አጉይ መነጽሮች፣ ወታደራዊ አልባሳት፣ በጨለማ የሚያሳዩ መነፅሮች፣ ወዘተ) ይዘው ወደ ስራ መሰማራትዎ ለእስር የመዳረገዎን እድል ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል ልብ ይበሉ።
  • ሁልጊዜ ትክክለኛ እና ህጋዊ የሆኑ ሰነዶችን (ለምሳሌ የፕሬስ መታዎቂያዎች፣ የመንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት፣ ቪዛ፣ ወዘተ) መያዘዎን ያረጋግጡ።
  • ሙሉ ሀይል ያለው የእጅ  ስልክ፣ የተወሰነ ገንዘብ፣ የሚወስዱትን ማንኛውንም መድሃኒት እና እንደ የመጠጥ ውሃ፣ ቀላል ሀይል ሰጪ ምግቦች እና ሞቃት ልብሶች ያሉ መሰረታዊ አቅርቦቶችን ይዘው ይሂዱ፡፡
  • አላባብሰዎትን ካሉብተ ሁኔታ ጋር ተስማሚ ያድርጉ፡፡ በፖሊስ ከተያዙ፣ ለተወሰነ ጊዚያት አንድ አይነት ልብስ ብቻ ሊለብሱ የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡
  • ለስር ከተዳርጉ፣ ምላሽዎ ምን አይነት ሊሆን እንደሚግባ ያስቡ፡፡ የፖሊስ መኮንኖች፣ እንደ ሁኔታው እና እንደቦታው  አይነት፣ ሀይለኞችና  ጠብ-አጫሪዎች  ሊሆኑብዎ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ ፡፡
  • መሳሪያዎችዎን ላለመቀማት ሲሉ፤ ጥቂትና አስፈላጊ የሆኑትን ብቻ ይውሰዱ ፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን የሲፒጄ የስጋት ምዘና(Risk Assessment)ቴምፕሌት ይጎብኙ።

የመረጃ ልዉዉጥ

  •  ለስር ቢዳረጉ፣ ሊጠሩልዎት የሚችሉ ሕጋዊ ተወካይን ለይተው ያዘጋጁ። ስማቸውን እና የሚገኙበትን ስልክ ቁጥር በስልክዎ ላይ እንዲሁም በወረቀት ላይ እና/ ወይም በክንድዎ ላይ ጽፈው ያስቀምጡ።
  • በውጭ አገር የሚሰሩ ከሆነ፣ የኢምባሲዎን/ የቆንስላ ጽ/ቤትዎን የድንገተኛ ጊዜ መረጃ በስልክዎ ውስጥ መዝግበው ይያዙ።
  • በተቻለ መጠን ብቻዎን ሆነው መስራትን ያስወግዱ፡፡ ብቻዎን ሆነው እየሰሩ ቢታሰሩ፣ ድምጸዎን ለማሰማት እና አቤቱታዎን  ለማቅርብ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።
  • የመታሰር/በቁጥጥር ስር የመዋል እጣ ከገጠመዎት፣ ከቢሮዎ፣ ከቤተሰብዎ ወይም ከጓደኞችዎ ጋር መደበኛ የመገናኛ ዘዴ ያዘጋጁ። በየምን ያህል ጊዜ ሊያገኟቸው እንዳሰቡና፣ ካሰቡት ጊዜ በላይ ቢቆዩ ደግሞ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና መቼ እንደሚመለሱ  ያሳውቋቸው።

በምደባ ወቅት

  • ባንድ ቦታ፣ በተለይ ደህንነቱ  አስተማማኝ ባልሆነ አካባቢ (ለምሳሌ ከፖለቲካ ህንፃ ውጭ በሆነ አጠራጠሪ ቦታ)፣ ብዙ ጊዜ ላለማቆየት ይሞክሩ።
  • በብዙ ሀገሮች የሚገኙ የፖሊስ መኮንኖች በፊልም መቀረጽ ወይም ፎቶ መነሳት አይወዱም። ፖሊስ ባለበት ቦታ ወይም አካባቢ ሲሰሩ ይህንን ልብ ይበሉ።
  • የመታሰርን  አጋጣሚ ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ እንደ የጦር መሣሪያ፣ አልኮል፣ አደንዛዥ ዕፅ ወይም ሌሎች አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮችን በጭራሽ አይያዙ ፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉ/ከታሰሩ

  • የፖሊስ መኮንኑ፣ እርስዎን በቁጥጥር ስር ከማዋሉ በፊት፣  እየታሰሩ መሆነዎትንና ለምን እንደሚታሰሩም ሊነግርዎት ይገባል። ወደ እስር የሚወሰዱበትን ቦታ፣ ጊዜ እና ሁኔታ በጥሞና ያስተውሉ።
  • ሁሌም ተረጋግትውና  ትሁት ሆነው ይቅረቡ። ኮፍያ እና/ ወይም የፀሐይ መነጽር አድርገው ከነበር ያውልቁ። ከተቻለ፣ ከባለስልጣኑ ጋር የአይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ፤ ተቃውሞም አያሳዩ።
  • የሚያስረዎን ሰው ፎቶግራፍ አለማንሳት ወይም ፊልም አለመቅረጽ ይመከራል– ይህን ማድርግ፣ ፖሊስን አስቆጥቶ ካሜራዎ እንዲጎዳ ወይም እንዲወረስ ሊያደርግ ይችላል።
  • በቻሉት መጠን፣ ሻንጣዎን መሳሪያዎን እና ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎችዎን ማየት በሚችሉበት ቦታ ላይ ያስቀምጡ።
  • እንደ አስም ወይም የስኳር በሽታ ያሉ የጤና ችግር ካለበዎት፣ ሁኔታውን ለፖሊስ ያሳውቁ። የጤናዎን ሁኔታዎን ለመቆጣጠር መድሃኒት የሚወስዱ ከሆነ፣ ልክ እንደተያዙ ወዲያውኑ ለፖሊስ ይንገሩ።
  • የአእምሮ ጤና ችግሮች ታሪክ ካለበዎት ወይም በወቅቱ የአእምሮ ጤንነት ችግሮች ካጋጠመዎት ለፖሊስ ይንገሩ።
  • በተቻለዎት መጠን፣ እርስዎን ለማሰር ስለተሳተፉ የፖሊስ መኮንኖች ዝርዝር ማለትም ስለስማቸው፣ ስለመለያ ቁጥሮቻቸው፣ ስለሚሰሩባቸው ክፍሎች፣ እና በቀላሉ ሊታወቁ ስለሚችሉ ምልክቶች (ለምሳሌ ንቅሳቶች ፣ የፊት ፀጉር እና የመሳሰሉት)ማስታወሻ ይያዙ።
  • ስለመታሰርዎ ምስክር ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦች  በዙሪያዎ ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ አካባቢዎን በትኩረት ይቃኙ፡፡ አስፈላጊ ከሆነ፣ አቤት እንዲሉለዎት ፍንጭ ይስጧቻው።
  • የአከባቢውን ቋንቋ የማይናገሩ ወይም የማይችሉ ከሆነ ተርጓሚ እና / ወይም ጠበቃ ወይም የህግ ተወካይ እስከሚያገኙ ድረስ ማንኛውንም ሰነድ አይፈርሙ ወይም ምንም ነገር አይመኑ፡፡
  • የፖሊስ መኮንኑ ህገ-ወጥ እቃዎችን ደብቀዋል ብለው ከጠረጠሩ፣ ሊበረብሮዎት፣ ሊፈትሹዎት ፣ ሊደባብሱዎት ወይም ደግሞ ልብስዎን አስወልቅው ሊፈትሹዎት ይችላሉ። ልብስዎን አስወልቀው የሚፈትሹዎት ከሆነ፣ ለህዝብ እይታ ተጋላጭ ባልሆነ ሁኔታ መከናወን አለበት። እንደዚህ አይነት ፍተሻ ሲካሄድ፣ ሁሌም በርካታ መኮንኖች መገኘት ይኖርባቸዋል። ሴቶች ጋዜጠኞች ደግሞ፣ በሴት ፖሊሶች ብቻ ካልሆነ በስተቀር፣ ራቁታችንን አንፈተሽም የሚል ጠንካራ ተቃውሞ ማቅረብ አለባቸው።
  • የፖሊስ መኮንኖች፣ እንዳሉበት የቦታ ሁኔታ፣ አስፈራርትው እና/ወይም አስግድደው ወንጀል ስርቻለሁ  ብለው እንዲይያምኑ ለማድረግ ሊሞክሩ ይችላሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥመዎት፣ ውስጥዎት ያለውን ውነት ይዘው ሙጭጭ ይበሉ፤ ያላደረጉትን ማንኛውንም ነገር ከመቀበል ተቆጥበው፣ የሕግ ድጋፍ እስኪመጣለወት ድረስ  ይጠባበቁ።
  • በማንኛውም የፖሊስ መኮንን ጥቃት ከደረሰብዎት፣ ስደረሰበዎት ጉዳት፣ ስላገኙት ህክምና እና ስለማንኛውም የሆስፒታል ጉብኝትዎ  ማስታወሻ  ለመያዘ ይሞክሩ። የጉዳት አድራጊዎችን ስሞች እና የማንነታቸውን መግለጫዎች መዝግበው ለመያዝ ይሞክሩ።

የሲፒጄ የመስመር ላይ ደህንነት ኪት(Safety Kit)ለጋዜጠኞች እና ለዜና ክፍሎች የሕዝባዊ አመፅ (civil unrest) መዘገብን ጨምሮ በአካላዊ፣ በዲጂታል እና በስነ-ልቦና ደህንነት ምንጮች እና መሳሪያዎች ላይ መሰረታዊ የደህንነት መረጃዎችን ይሰጣል። ጋዜጠኞች እርዳታ ከፈለጉ ሲፒጄን ይህን ኢሜል [email protected] ግንኝነት መፍጠር ይኖርባቸዋል።