የ2013 የኢትዮጲያ ምርጫ፤ የጋዜጠኞች የደህንነት ኪት

ግንቦት 16፣ 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ፣ በዋናዋ ከተማ አዲስ አበባ የሚገኙ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ተሰልፈው። ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ፣ በ2013 ማብቂያ ላይ ድምጽ ይሰጣሉ። (ኤ.ፒ/ ሙሉጌታ አየነ)

በመላው ሀገሪቱ ውጥረት በነገሰበት ሁኔታ፣ በመጭው ሰኔ አጋማሽ አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ፣ ኢትዮጵያ ቀን ቆርጣለች። በትግራይ ውስጥ በህዳር ወር የተከሰተው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው። የሚዲያ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ በሌሎች በርካታ ክልሎችም፣ በብሔሮችና ጎሳዎች መካካል በሚፈጠር ግጭት እና በተቃውሞዎች የተነሳ፣ መጠነ-ሰፊ ነውጦች እና ዘግናኝ አደጋዎች ታይተዋል። 

የሲፒ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ከህዳር 22፣ 2013 ጀምሮ፣ ቢያንስ ሰባት የሚሆኑ ጋዜጠኞች ዘብጥያ ወርደዋል፤ በሲፒጄ እና በሚዲያ ዘገባዎች እንደተስነደው፣ ባለስልጣናት፣ የሰላ ሂስ በሚያካሂዱ የዜና አውታሮች ላይ ጫና እያካሄዱ ነው። ባለፈው መጋቢት ወር፣ የኢትዮጲያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን፣ ሰይመን ማርክስ የተባለውን የኒው ዮርክ ታይምስ የስራ ፈቃድ ከስረዘ በኋላ ክሀገር አባሮታልየሚዲያ ዘገባዎች እንዳመለከቱት፣ የተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት፣ አሶሼትድ ፕሬስን ጨምሮ፣ ስለ ትግራዩ ግጭት ለዘገቡ የሚድያ አውታሮችና የዜና ወኪሎች ማስጠንቀቂያዎችን ልኳል።  

በመላው ሀገሪቱ ምርጫውን የሚዘግቡ ጋዜጠኞች የተለያዩ አደጋዎች/ስጋቶች/ችግሮች ሊገጥሟችው እንደሚችሉ ልብ ሊሉ ይገባል። ስጋቶቹም የሚከተሉትን (ግን በእነዚህ ብቻ ያልተውሰኑ) ያካትታሉ፤ ግንኙነትን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት፤ በአመጽ ተቃውሞ፣ በጎሳ ግጭት ወይንም ወታደራዊ ግጭት መሃል መጠመድ፤ አካላዊ ትንኮሳ እና ማስፈራራት፤ ነገር መጫርና ማብሽቅ፤ እና ሰዓት እላፊን ጨምሮ በመንግስት የሚጣል የእንቅስቃሴ ገደብ። 

የሲፒጄ የአደጋ ጊዜ ቡድን፣ ይህንን የምርጫ የጥንቃቄ ኪት ምርጫውን ለሚዘግቡ ጋዜጠኞች አጠናቅሯል።  ኪቱም ለአዘጋጆች፣ ለሪፖርተሮች እና ለፎቶ ጋዜጠኞች ስለ ጠቅላላው የምርጫ ኡድት እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው እና አካላዊና ዲጅታል ስጋቶችን እንዴት መቀንሰ እንደሚችሉ መረጃ ይሰጣል።  

የዚህን ሴፍቲ ኪት ፒዲኤፍ ቅጂ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ማውረድ ይችላሉ።

ማውጫ

ግንኙነቶችና ግብአቶች/ምንጮች

ኢትዮጵያ ውስጥ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ጋዜጠኞች እርዳታውን በሚከተሉት የኢሜል አድራሻዎች ማግኘት ይችላሉ፤ በሲፒጄ የአደጋ ጌዜ ፕሮግራም በኢሜል አድራሻ፤ electionsafety@cpj.org  ወይም በሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም በኢሜል አድራሻ፤  cpjafrica@cpj.org.

የሲፒጄ የግብዓት ማዕከል፣ የቅድመ ስራ ስምሪት ዝግጅትን እና የድህረ-ሁነት እርዳታን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎችና መመሪያዎች አሉት። 

አካላዊ ደህንነት፤ ጠቅላላ የደህንነት ምክር

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16 ቀን፣ 2010 ዓ.ም. ድጋፉን ሊገልጽላቸው ለወጣው ህዝብ እጆቻቸውን በማወዛወዝ ሰላምታ ሲስጡ። (ኤ.ፒ/ ቤን ኩርቲስ)

አካላዊ ደህንነት፤ ከፖለቲካዊ ስብሰባዎች እና ህዝብ ከተሰበሰበባቸው ዝግጅቶች ሪፖርት ማድረግ

የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች በፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ ህዝብ ከተሰበሰባበቸው ዝግጅቶች ወይም ከምርጫ ጋር በተያያዙ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በሚሳተፉበት ወቅት በሁከትና/ ወይም አመጽ መሃል ሊገቡና የጥቃቱም ሰለባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማወቅ አለባቸው። ይህ ደግሞ በተለይ በብሔሮች መካከል አለመግባባት በሚፈጠርባቸው እና  የታጠቁ ቡድኖችና ሚሊሻዎች በሚንቀሳቀሱባቸው ወረዳዎች እና ዞኖች ሊከሰት እንደሚችል ሊገነዘቡ ይገባል።

እነዚህን አደጋዎች ለመቀነስ እንዲቻል፣ የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች የሚከተሉትን የደህንነት ምክሮች ማጤን አለባቸው፤

በቦታው ላይ

የቦታ አያያዝንና ሁኔታን ስለመገንዘብ

ሚያዚያ 24 ቀን 21013 ዓ.ም አንድ የአማራ ሚሊሺያ አባል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ ላይ ፎቶ ሲነሳ።

አካላዊ ደህንነት፤ ሕዝባዊ አመፅ ባለባቸው እና ሩቅ ስፍራዎች ውስጥ መሥራት

(ኤ.ፒ/ ቤን ኩርቲስ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በ 2010 ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ ግጭቶች፣ ህዝባዊ አመጾች እና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እየተከሰቱ ሲሆን፣ ይህንን ተክትሎም የጥላቻ ንግግሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎችም ታሪካዊ አለመተማመንን ሲያቀጣጥሉት በጎሳና ፖለቲካ ቡድኖች መካከል ያለውን ውጥረትን ሲያጦዙት ቆይተዋል። አከባቢያዊ ወይም ክልላዊ አለመረጋጋቶችን ሲያነሳሱ ከነበሩ አይነትኛ ምክንያቶች መካከልም የመሬት ይገባኛል ግጭቶች፣የግጦሽ መሬት የመብት ጥያቄዎች ፣ የተማሪዎጭ አመጾች እና የሃይማኖት ግጭቶች ይገኙበታል፡፡

ሁከቱን ምን እንደቀሰቀሰውና ምን እንደሚያራግበው መረዳት፣ ሊፈጠሩ የሚችሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን አደጋዎችን ለይቶ ለማወቅና ለመቀነስ ይረዳል።  የሁከቱ መንሰኤ፣ አልፎ አልፎ ብልጭ ድርግም የሚል የክልል ድንበሮች (በቅርቡ ሶማሌ እና አፋር ውስጥ እንደታየው) መካከል ያለ ግጭት ነው? ወይስ፣ ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ (በኦሮሚያ ውስጥ በቅርቡ እንደተስተዋለው) ጥቃት ነው?  ወይስ ደግሞ ሲብላላ የቆየ ብሄር-ተኮር (በድሬዳዋ እና በሐረር በቅርቡ እንደተከሰተው) ውጥረት ውጤት ነው? 

የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች፣ የትኛውም ቦታ (ትልቅ ከተማም ይሁን ሩቅ ቦታ የሚገኝ ወረዳ) ድንገተኛ የረብሻ አመጽ ሊያስተናግድ እንደሚችል ሊገነዘቡ ይገባል፤ ይህ ደግሞ፣ አብዛኛውን ጊዜ ያለበቂ ወይንም ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ሊከሰት ይችላል።

አስቀድሞ ማቀድ

መጓጓዣ እና መገልገያ መሳሪያዎች

የአካባቢ ደህንነት እና ግንዛቤ

የፍተሻ ኬላዎች

በተለይ ህዝባዊ አመፅ እና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ባሉባቸው አካባቢዎች በወታደሮች፣ በፖሊስ ኃይሎች እና በአካባቢው ሚሊሻዎች የሚካሄዱ የፍተሻ ጣቢያዎችን በኢትዮጵያ አውራ ጎዳናዎች እና መንገዶች ላይ ማየት የተለመደ ክስተት ሊሆን ይችላል።

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተሽከርካሪዎች እና ሰራተኞቻቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኬላዎች እና በተዘጉ መንገዶች ላይ የጥቃት ዒላማ ሆነዋል። በዚህ ረገድ፣ ትግራይ ወስጥ ኤም.ኤስ.ኤፍ ሰራተኞች ላይ፤  በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ደግሞ፣ በአየርላንድ የእርዳታ ኤጀንሲ (GoAL) ሰራተኞች ላይ የደርሰው ተጠቃሽ ነው። በተጨማሪም፣ ሲኤንኤን በቅርቡ እንደዘገበው፣ ከኢትዮጵያ ጦር ፈቃድ ያገኘ የጋዜጠኞች ቡድን ወደ ትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች እንዳይገባ በኤርትራ ወታደሮች ተከልክሏል ፡፡

አጠቃላይ ደህንነት

ምርጥ ተሞክሮዎች

ሊያስዎግዷቸው የሚገቡ፤

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች፣ ግንቦት 17 ቀን፣ 2002 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሀገር አቀፉን የምርጫ ድል ሲያከብሩ።  (ኤ.ፒ/ አኒታ ፓዎል)

አካላዊ ደህንነት፤ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ከሚነሱ የተቃውሞ ቦታዎች ሪፖርት ማድረግ/መዘገብ

በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ እንደታየው ሁሉ፣ ሕዝባዊ ሰልፎች በማንኛውም የምርጫ ዑደት ወቅት ሊከሰቱ እና በፍጥነት/በድንገት ወደሚዘገንን ሁኔታ ሊለወጡ ይችላሉ። እንዲህ ዓይነቱን ተቃውሞ የሚዘግቡ የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች ለተለያዩ አደጋዎች ሊጋለጡ ይችላሉ። ይኽም የሚሆነው፣ በተቃውሞ ሰልፈኞች፣ በፀረ-ተቃዋሞው ሰልፈኞች እና ሰልፈኞችን ለመበተን ጥይት በመተኮስ እና አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም በየሚታወቁ በፀጥታ ኃይሎች መካከል በሚነሳ ብጥብጥ የተነሳ ነው፡፡ እንደ ትግራይ ባሉ የግጭት ቀጠናዎች፣ ቀላል መሳሪያዎች ጥቅም ላይ አይውሉም ማለት አይቻልም ፡፡

አደጋውን ለመቀነስ ይቻል ዘንድ የሚዲያ ሰራተኞች የሚከተሉትን የደህንነት ምክሮች ማጤን ይገባቸዋል፤

ማቀድ

አለባበስ እና መሣሪያዎች

ጥቅምት 13፣ 2012 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ ቡድን አባላት፣ ጃዋር መሃመድ ከተባሉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ቤት ፊት ለፊት መፈክር በማሰማትና በመጮህ ድጋፋቸውን ሲገልጹ:: (ኤ.ፕ/ ሙሉጌታ አየነ)

የቦታ አያያዝን እና የሁኔታዎች ግንዛቤ

የአስለቃሽ ጋዝን መቋቋም

የአስለቃሽ ጋዝ ጥቃት ማስነጠስ፣ ማሳል፣ መትፋት፣ ማልቀስ እና መተንፈስን የሚገታ ንፍጥ እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ፣ በአስለቃሽ ጋዝ የተጠቁ ግለሰቦች፣ ሊያስታውኩ እና መተንፈስም ሊያቅታቸው ይችላል፡፡ እንደነዚህ አይነት ምልክቶች፣ የሚዲያ ሰራተኞችን፣ በአየር ወለድ የቫይረስ ጠብታዎች አማካይነት ለሚመጣ ለኮርኦቫይረስ በሽታ እስከ መጋለጥ ሊያደርሳቸው ይችላል፡፡ በኮቪድ-19 ተጋላጭ ምድብ ውስጥ በተዘረዘሩ እንደ አስም ባሉ የመተንፈሻ አካላት ችግር የሚሠቃዩ ግለሰቦች፣ ህዝባዊ ሁነቶችን ከመዘገብ ሊቆጠቡ ይገባል፡፡ የዚህ አይነት ችግር ያለባቸወ የሚዲያ ሰራተኞች፣ የአስለቃሽ ጭስን የመጠቀም አዝማሚያንም ሲያዩ፣ ተቃውሟቸውን ማሰማት አለባቸው። 

በተጨማሪም፣ በኤን. ፕ. አር (NPR) እንደተገለጸው እና መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ አስለቃሽ ጭስ፣ ግለሰቦችን፣ እንደ ኮሮናቫይረስ ላሉ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ይበልጥ ተጋላጭ  ሊያደርግ ይችላል።

የአስለቃሽ ጋዝ ተጋላጭነት ስለመቋቋም  እና የሚያስከትሉትን የአስከፊ ውጤቶችን በተመለከተ ተጨማሪ መመሪያ ለማግኘት፣ እባክዎን የሲፒ.ጄን  የሲቪል ዲዝኦርደር ምክረ-ሀሳብ ይመልከቱ ( CPJ’s civil disorder advisory) ይመልከቱ። 

አካላዊ ትንኮሳ እና ጥቃት

በሮይተርስ ፎቶግራፍ አንሺ ቲክሳ ነገሪ ላይ እንደተከሰተው የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች በቦታው ላይ ሆነው በቀጥታ በሚዘግቡበት ጊዜ፣ በተቃዋሚዎችም ሆነ በፀጥታ ኃይሎች የአካል ጥቃት አደጋ ሊደርስባቸው እንደሚችል ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጠብ አጫሪነት ሲገጥመዎት፣ የሚከተሉትን የደህንነት ምክሮችን ለመጠቀም ያስቡ፤

አካላዊ ደህንነት፤ ከነውጠኛ ማህበረስብ መሀል ሆኖ ሪፖርት ማድረግ

በምርጫ ዑደት ወቅት፣ የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች ለሚዲያ ሰዎች፣ ከሙያው ውጭ ለሆኑ ሰዋቸ ወይንም ደግሞ ለሚዲያ የጠላትነት ስሜት ባላቸው አካባቢዎች ወይም ማኅበረሰቦች መሃል ሆነው መስራት ሊጠበቅባቸው ይችላል። የዚህ አይነት ሰሜት ሊፈጠር የሚችለው፣ አንድ ማህበረሰብ የተሰማራባቸነ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች (ለምሳሌ የጦር መሳሪያ ወይም የሰዎች ዝውውር) ለመደበቅ በሚፈልግበት ጊዜ ነው፡፡ ስለሆነም፣ እንደዚህ አይነት ማህበረሰቦች፣ ጋዜጠኞችን ሊያጋልጡን ይችላሉ በሚል ፍርሃት፣ እንደ ስጋት ሊመለከቷቸው ይችላሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ፣ ሚዲያው በትክክል አይወክለንም የሚል ስሜት አላቸው፤ በአሉታዊ መልክ ነው ስለእኛ የሚዘግበው ብለው የሚያምኑ ወግኖችም አሉ። 

አደጋዎችን መቀነስ ማስቻል 

አካላዊ ደህንነት፤ ኮቪድ-19ን ከግምት ውስጥ ማስገባት

የምርጫ ዝግጅቶች እና ተዛማጅ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት መኖሩ የተለመደ ነው፤ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ደግሞ በጣም ፈታኝ ነው። የህብረተሰቡ አባላት የፊት መሸፈኛ ጭምብል ላይለብሱ ይችላሉ። የሚዲያ ሰራተኞችም ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር በትንሽ ስፍራ ተፋፍገው መስራት ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ መተፋፍግ፣ ጋዜጠኞችን ለቫይረሱ ጠብታዎች ሊያጋልጣቸው ይችላል። ከዚህም በላይ፣ ነውጠኛ  ሆኑ የማህበርሰቡ አባላት ሊሰድቧቸው፣ የአካላዊ ጥቃት ሊደርስባቸው እና  እላያቸውም ላይ ሊስሉባቸዉና ሊያነጥሱባቸው ይችላሉ፡፡

የሚጮሁ ወይም የሚዘምሩ ሰዎች የቫይረሱን ጠብታዎች ሊያዛምቱ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ፤ ይህም፣ የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች ለኮሮናቫይረስ በሽታ የመጋለጣቸውን ደረጃ ከፍ ያደርገዋል። 

ስለኮቪድ-19 ወረርሽኝ አዘጋገብ ተጨማሪ ዝርዝር  መመሪያ  ለማግኘት፣ የሲፒጄን የኮቪድ-19 የደህንነት ማማከሪያ  (CPJ’s COVID-19 safety advisory) (የአማርኛው ትርጉም) ይመልከቱ።

ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ፣ በደቡብ ምስራቅ በምትገኝ አዳማ በተባለች ከተማ ውስጥ፣ ካሌብ አለማየሁ የተሰኘ የአንድ ኢንተርኔት ካፌ ባለቤት፣ ሚያዚያ 6፣ 2013 ዓ.ም ኮምፒውተር ሲነካካ።  (ኤ. ኤፍ. ፒ/ ሶላን ኮፊ)

የዲጂታል ደህንነት፤ ጠቅላላ ምርጥ ተሞክሮዎች

የዲጀታል ደህነነት፤ መሳሪያዎቸዎን ለፖለቲካዊ የድጋፍ ሰልፍ ማዘጋጀት

አንድን የድጋፍ ሰልፍ ከመዘገብዎ በፊት የመሳሪያዎን እና የመረጃዎን ደህንነት ለመጠበቅ እርምጃዎችን መውሰድ ሌሎች ስለ እርስዎ እና ስለ ምንጮችዎ መረጃ የማግኘት እድላቸውን ይቀንሰዋል ፡፡

ምርጥ ተሞክሮዎች

የዲጂታል ደህንነት፤ ለግንኙነት መቋረጥ መዘጋጀት

በሲፒጄ እንደተሰነደው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በተለይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በሚከሰትበት ወቅት፣ የኢንተርኔት የግንኙነት መቋረጦች የተለመዱ ናቸው። በሰኔ 2012፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ፣ ኢንተርኔት ተዘግቶ ነበር፤ እንዲህ አይነት የግንኙነት መቋረጦች በየክልሉም የተለመዱ ናቸው። በህዳር 2012 ከተፈጠረው የትጥቅ ግጭት አንስቶ፣ የትግራይ ክልል የኢንተርኔት መቋረጥ አጋጥሟታል ሲል ሲፒጄ ሰንዷል፡፡ የግንኙነት መቋረጥ ከጥቂት ሰዓታት እስከ ወራቶች ሊቆይ የሚችል ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መጥፋትን ሊያካትት ይችላል፤ በግንኙነቶኝ መቋረጥ ወቅት መሥራት ውስብስብ ሊሆን ቢችልም፣ ጋዜጠኞች እራሳቸውን ለዚህ ሁኔታ በማዘጋጀት፣ ሊወስዷቸው የሚችሏቸው እርምጃዎች አሉ

አጠቃላይ የዲጂታል ደህንነት ምክር

ለግንኙነቶች መጥፋት/መቋረጥ መዘጋጀት

በይነመረብ መዘጋት ወቅት፣ በይነመረብን የማግኘት እድል ያላቸው እንድ ኤምባሲ ወይም ባንኮች ያሉ መስርያቤቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችን ወይም አገልግሎቶችን ለየትው ይወቁ፡፡ በይነመረብ ላይ ያለን መረጃ ሊያገኙልዎ ይችሉ እንደሆነ አስቀድመው ያነጋግሩዋቸው።

ትክክለኛዎቹን መሳሪያዎች መምረጥ

የመስመር ላይ መሳሪያዎች እና አገልግሎቶች ለደህንነት ጥሰቶች የተጋለጡ ናቸው። ጋዜጠኞች፣ በተለይ እንደ የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያዎች ያሉ የግንኙነት መሳሪያዎችን በተመለከተ፣ የቅርብ ጊዜውን የዲጂታል ደህንነት መረጃ እንዲተገብሩ ይመከራሉ፡፡ የሚከተለው ምክር ግንቦት 2013 ጀምሮ የሚያገለግል ነው፡፡

በግንኙነት መጥፋት ወቅት

ከግንኙነቶች መጥፋት በኋላ

የዲጅታል ደህንነት፤ እራስን ከማስገር (Phishing) ስለመከላክል

የማስገር ዘመቻዎች፣ በምርጫ ወቅት ሊጨምሩ ይችላሉ።  ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ተቋማት ከዚህ ቀደም የተራቀቁ የአስጋሪ የጥቃት ሰለባዎች ሆነው ቆይተዋል።  ሲቲዝን ላብራቶሪ እና ግላዊነት ኢንተርናሽናል (Citizen Lab and Privacy International) እንደዘገበው፣ የዚህ አይነቱ ጥቃት፣ በየመሣሪያዎች ላይ እየተጫኑ ላሉ የንግድ ስፓይዌሮች ምክንያት ሆኗል። ሰለ ምርጫ፡ ዘመቻው የሚዘግቡ ጋዜጠኞች በኢሜል እና በመልዕክቶች የተላኩ ሰነዶች እና ሊንኮች ሲያጋጥሟቸው የተለየ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ። በዚህ ረገድ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን የያዙ ምክሮች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።

አጠቃላይ ምርጥ ተሞክሮዎች

የዲጂታል ጥንቃቄ፤ የመስመር ላይ ጥቃት እና የተሳሳተ መረጃ ዘመጃዎች 

በመርጫ ወቅት፣ በተለይ አዘጋገቡ መንግስትን በጣም በሚያጥላላ ወይም በጣም በሚደግፍ ሁኔታ ተቃኝቶ በሚሰራብት ጊዜ፣ በሲፒጄ እንደተሰነደው፣ በእነሱ ላይ ያነጣጠረ ጥቃትን ጨምሮ፣ ጋዜጠኞች የመስመር ላይ የትንኮሳ ሰለባ የመሆናቸው አጋጣሚ ከፍተኛ ነው። በመስመር ላይ፣ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎችም ሆን ተቃዋሚዎች ንቁ ተሳታፊዎች ናቸው።  ትግራይ ውስጥ ሆነው የሚዘግቡ ጋዜጠኞች የመስመር ላይ ጥቃት እና ሀሰታኛ መረጃን ታሰራጫላችሁ የሚል ክስ ሊግጥማቸው እንደሚቸል ልብ ሊሉ ይገባል። የዲጅታል መብት ኔትዎርክ ለአፍሪካ የተሰኘው ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት እንደዘገበው፣ ጥቃቶች፣ የተቀነባበሩ የትዊተር ዘመጃዎችን አቋቁመው በሚያጧጡፉ የመንግስት ተቃዋሚ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማሕበርስቦች ሊፈጸሙ ይችላሉ። ጋዜጠኞች እራሳቸውንና አካውንቶቻቸውን ከጥቃት በተሻለ ለመከላከል የሚያስቸሏቸው የተለያዩ ዘዴዎች አሉ። 

የጥቃትን ስጋት ለመቀነስ

በጥቃት ጊዜ

ማጠቃለያ፡ የአዘጋጆች የደህንነት ማረጋገጫ ዝርዝር

የዜና አዘጋጆች፣ የሚዲያ ሰራተኞችን በአጭር ጊዜ ማሳሳቢያ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ኩነቶችን እንዲዘግቡ ሊጠይቋቸው ይችላሉ፤ አዘጋጆቹ ይህንን በሚያደርጉበት ጊዜ፣ የሚዘገበው ሁነት በድንገት ወደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል፣ ሁነቱ የሚዘገበው በጣም ከራቀ አካባቢ ሊሆን እንደሚችል ወይም ደግሞ አካባቢው በብሔር መቆራቆሰና ግጭት የሚታምስ ሊሆን እንደሚችል ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።  ይህ የደህንነት ማረጋገጫ ዝርዝር በሠራተኞች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ ሊነሱ የሚችሉ ዋና ዋና ጥያቄዎችን እና መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች አካትቷል።

ጠቃሚ ማስታወሻ፤ የሚከተሉት ጠቃሚ ነጥቦች እንደ መፍትሄ ፈላጊዎች፣ ቦታ አመላካቾች እና የትርጉም ስራ በሚስሩ የአካባቢው ወገኖች ዘንድ ሊታወቁ ይገባል::

ስሰራተኞች ሊታሰቡ/ግምት ውስጥ ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች 

መሳሪያና ትራንስፖርት

ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገባቸው አጠቃላይ ጉዳዮች 

ስለ ስጋት ዳሰሳ እና እቅድ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ የሲፒጄን የመረጃ/ የግብዓት ማዕከል ይመልከቱ 

Exit mobile version