የዲጂታል ደህንነት ኪት

Artwork: Jack Forbes

ምስል- ጃክ ፎርብስ

የዲጂታል ደህንነት ኪት

በመጨረሻ የተሻሻለው፣ ሚያዚያ 13 2013 ዓ.ም

ጋዜጠኞች የወቅቱን የዲጂታል ደህንነት ዜናዎችን እና እንደ ምንተፋ (hacking)፣ ፊሺንግ (phishing) እና ክትትልን (surveillance) ባሉ ስጋቶች ላይ የሚወጡ ወቅታዊ መረጃዎችን በመከታተል ራሳቸውንና የመረጃ ምንጮቻቸውን መከላከል አለባቸው፡፡ ጋዜጠኞች ሃላፊነት ሰለወስዱበት መረጃና መረጃው ባልተገባ ሰው እጅ ቢገባ ምን ሊፈጠር እንደሚችል በማሰብ አካውንቶቻቸውን፣ መሣሪያዎቻቸውን፣ ግንኙነቶቻቸውን እና የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎቻቸውን ለመከላከል ተገቢ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው፡፡

የሲፒጄ የዲጂታል ደህንነት ኪት በተጨማሪም በስፓኒሽኛበፈረንሳይኛበሩሲያኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች ይገኛል።

ይዘቶች

አካውንቶቻችሁን ስለመጠበቅ

ፊሺንግ

የመሣሪያ ደህንነት

የተመሰጠሩ ግንኙነቶች

ደህንነቱ የተጠበቀ የበይነመረብ አጠቃቀም

ድንበሮችን ማቋረጥ

አካውንቶቻችሁን ስለመጠበቅ

አካውንቶቻችሁን ለመጠበቅ፤

ጋዜጠኞች የተለያዩ የመስመር ላይ አካውንቶችን ይጠቀማሉ፤ እነዚህም አካውንቶችም፣ ከራሳቸው፣ከስራ ባልደረቦቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው የግልና የስራ ጉዳዮች ጋር የተሳሰሩ መረጃዎችንና የመረጃ ምንጮችን ያካትታሉ::  የእነዚህን መለያዎች ደህንነት ማረጋገጥ፣ አዘዎትሮ ምትክ ማስቀመጥ እና መረጃዎችን ማጥፋት እነዚህን መረጃዎች ለመታደግ ይረዳል::

ፊሺንግ

ጋዜጠኞች ብዙ ጊዜ ሕዝባዊ መገለጫዎች አሏቸው። ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኝት ሲሉ፣ የመገኛ ዝርዝሮቻቸውን ለሌሎች በይፋ ያጋራሉ። ባላጋራዎቻቸው ደግም፣ የጋዜጠኞችን መረጃና የመረጃ ቁሳቁሶችን ለማግኘት ሲሉ፣ ጋዘጠኞችን እራሳቸውን፣ የስራ ባልደረቦቻቸውን ወይም የቤተሰባቸውን አባል የፊሺንግ ጥቃት ዒላማ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህንንም የሚያድርጉት፣ ከሚያውቁት ሰው የተላኩ የሚመስሉ ኢሜሎች፣ የአጫጭር መልክቶች፣የብዙሃን መገናኛዎች ወይም የቻት መልዕክቶች በመጠቀም፣ ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲያጋሯቸው በማታለል ነው። በተጨማሪም፣ ተንኮል አዘል መረጃዎችን (malware)  የያዙ አገናኞችን( link) አውርደውም ኮምፒተራቸው ላይ እንዲጭኗችው ያደርጋሉ። የተለያየ ደረጃ ውስብስብስነት ያላችው ብዙ አይነት ተንኮል አዘል መረጃዎች እና ስፓይዌሮች (spyware) አሉ። ከነዚህ መካከልም፣ የተራቀቁ የሚባሉት ስፓይዌሮች፣ የርቀት የመረጃ መሳሪያዎችን በመጠቀም፣ ለጥቃት ፈጻሚዎቹ የሚፈልጉትን መሳሪያ እና በውስጡ የሚገኙ መረጃዎችን ከርቀት ለማሳየት የሚያስችል አቅም አላቸው።

የፊሺንግ ጥቃቶችን ለመከላከል፤

የመሣሪያ ደህንነት

ይዘቶችን ለማዘጋጀት እና ለማከማቸት እንዲሁም የመረጃ ምንጮችን ለማግኘት፣ ጋዜጠኞች የተለያዩ መሣሪያዎችን ይጠቀማሉ። ብዙ ጋዜጠኞች፣ በተለይም በግላቸወ የሚሰሩ ጋዜጠኞች፣ እቤታቸው ሆነው ሥራቸውን በሚሰሩበት ወቅት፣ አንድ ዓይነት መሣሪያዎችን ይጠቀማሉ። እንደዚህ አይነቱ አሰራር፣ መሳሪይዎቹ በድንገት ቢጠፉ፣ ቢሰረቁ ወይም ቢወሰዱ ብዙ መረጃዎችን ላደጋ ያጋልጣል። የኮምፒተርን የሃርድ ድራይቮች፣ የስልኮችን፣ የታብሌቶችን እና የውጭ ማከማቻ መሣሪያዎችን በመመስጠር፣ ሌሎች ሰዎች መረጃን ያለ የይለፍ ቃል ማግኘት እንዳይችሉ ማረጋግጥ ይገባል። በተለይ ደግሞ በጉዞ ላይ በሚሆኑበት ወቅት ይበልጥ መጠንቀቅ ይኖርበዎታል፡፡

የመሳሪያዎችዎን ደህንነት ለመጠበቅ፤

መሳሪያዎን ለማመስጠር፤

የተመሰጠሩ ግንኙነቶች

ጋዜጠኞች የተመሰጠረ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያዎችን ወይም መልዕክታቸውን የሚገባው ተቀባይ ብቻ እንዲያነበው የሚያስችል ኢሜልን የሚያመሰጥር ሶፍትዌርን በመጠቀም ደህንነታቸው በይበልጥ በተጠበቀ መልኩ ከመረጃ ምንጮቻቸውጋር መገናኘት ይችላሉ። አንዳንዶቹ የመመስጠሪያ መሳሪያዎች ከሌሎች ይልቅ ለመጠቀም ቀላል ናቸው፡፡ ምስጠራ፣ የመልዕክቶችን ይዘት ይጠብቃል፤ ነገር ግን የምስጠራ ኩባንያዎች ሜታዳታውን ማለትም እርስዎ መልዕክቱን መቼ እንደላኩት፣ ማን እንደተቀበለው እንዲሁም ሌሎች ገላጭ ዝርዝር መረጃዎችን ማየት ይችላሉ፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ይህንን መረጃ እንዴት እንደሚያከማቹ እና ባለሥልጣናት ስለመረጃዎቹ ሲጠየቋችወ፣ እንዴት ምላሽ እንደሚሰጡ የተለያዩ ፖሊሲዎች አሏቸው ፡፡

የተመረጡ የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያዎች ከጫፍ እስከ ጫፍ የምስጠራ አገልግሎትን ይሰጣሉ፣ ይህም ማለት፣ መረጃው ከላኪው ወደ ተቀባዩ በሚላክበት ጊዜ ሚስጥራዊነቱ እንዲጠበቅ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህን ለማድረግ፣ የሁለቱም ወገኖች አካውንቶች ተመሳሳይ መተግበሪያ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል ፡፡ እንዲያም ሆኖ፣ መልዕክት የሚልከውን ወይም የሚቀበለውን መሣሪያ መክፈት የሚችል ወይም ከመተግበሪያው ጋር ለተያያዘው መለያ የይለፍ ቃል ያለው ማንኛውም ሰው የመልእክቱን ይዘት መመንትፍ ይችላል፡፡ ሲግናል እና ዋትስአፕ ከጫፍ እስከ ጫፍ ምስጠራ ያላቸው እና በነባሪ እየሰሩ የሚቆዩ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያ ምሳሌዎች ናቸው፡፡

የተመሰጠረ ኢሜል ከመረጃ ምንጭ ወይም ከእውቂያ ጋር መረጃን ለመለዋወጥ የሚያስችል ሌላ አስተማማኝ መንገድ ነው፡፡ የተመሰጠረ ኢሜል ለመላክ እና ለመቀበል ሁለቱም ወገኖች አንድ አይነት ሶፍትዌሮችን ማውረድ እና መጫን አለባቸው፡፡

የተመሰጠሩ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያዎችን ለመጠቀም፤

ኢንክሪፕት የተደረገ (የተመሰጠረ) ኢሜል ለመጠቀም፤

ከኢሜል ምስጠራ ሶፍትዌር ምሳሌዎች የሚከተሉት ይገኙበታል፤ ጂፒጂ ስዊት ለማክ፣ጂፒጂፎርዊን ለዊንዶውስ እና ለሊነክስ። ሌሎች ደግሞ፣ተንደርበርድ  የኢንጂሜይል ቅጥያ እና ሜልቬሎፕ ይሰኛሉ።

ደህንነቱ የተጠበቀ የበይነመረብ አጠቃቀም

ስራቸውን ለማቀላጠፍ፣ ጋዜጠኞች ኢንተርኔትን ይጠቀማሉ፤ ነገር ግን በመስመር ላይ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለማንኛውም የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢ፣ ለበይነመረብ ካፌ ወይም በነፃ ዋይፋይ ለሚሰጧቸው ሆቴሎች ለማጋራት አይፈልጉ ይሆናል፡፡ ወንጀለኞች እንዲሁም የተራቀቁ ባላጋራዎች ደህንነታቸውን ያልጠበቁ ድረ-ገጽ ጣቢያዎችን ወይም ለህዝብ ክፍት የሆኑ የዋይፋይ ግንኙነቶችን በመጠቀም መረጃዎችን እንድሚሰርቁ  ወይም ጋዜጠኞችን እንደሚክታተሉ ማወቅ ተግቢ ነወ።

በይነመረብን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለመጠቀም፤

ምስል- ጃክ ፎርብስ

ድንበሮችን ማቋረጥ

ብዙ ጋዜጠኞች ሌሎች ሰዎች በኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች ሊያገኙባቸው የማይፈልጉትን የሥራና የግል መረጃ ይዘው ድንበር ያቋርጣሉ፡፡ ድንበር ጠባቂዎች መሣሪያዎን ከእይታዎ አርቀው ከውሰዱት፣ መሳሪያውን ለመበርበር፣ ማንኛውንም መለያዎች ለማየት፣ መረጃ ለመቅዳት ወይም ስፓይዌሮችን ለመጫን እድሉ ይኖራቸዋል፡፡ የአሜሪካን ድንበር የሚያቋርጡ ጋዜጠኞች “ይፋ የማደርገው ምንም ነገር የለም የሚለውን የሲፒጄ የደህንነት ማስታወሻ ማንበብ ይኖርባቸዋል፡፡

ከመጓዝዎ በፊት፤

ድንበር ላይ፤

ድንበር ላይ ማንኛውም መሳሪያ ከተወረሰ ወይም ሌላ መሳሪያ ከተሰካበት፣ ደህንነቱ እንደተጣሰና በውስጡ ያለው ማንኛውም መረጃ ተገልብጦ እንደተወሰደ ይቁጠሩት።

Exit mobile version